am_tn/2ki/03/13.md

2.7 KiB

ከአንተ ጋር ምን የሚያገናኘኝ ነገር አለ?

ኤልሳዕ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ንጉሡና እርሱ ምንም የጋራ የሆነ ነገር እንደሌላቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን እንደ ዐረፍተ ነገር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአንተ ጋር ምንም ጉዳይ የለኝም›› ወይም፣ ‹‹ከአንተ ጋር ምንም የምጋራው ነገር የለኝም››

በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው

እዚህ ላይ፣ ‹‹የሞዓብ እጅ›› የሞዓብን፣ ‹‹ቁጥጥር›› ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሞዓባውያን ቁጥጥር አሳልፎ ሊሰጣቸው›› ወይም፣ ‹‹በሞዓብ ሰራዊት እንዲያዙ ለማድረግ››

በፊቱ የቆምሁት የሰራዊት ጌታ ሕያው ያህዌን

‹‹በፊቱ የቆምሁት የሰራዊት ጌታ ያህዌ በእርግጥ ሕያው እንደ ሆነ፡፡ እዚህ ላይ ኤልሳዕ የያህዌን ሕያው መሆን እርግጠኝነት፣ ለኢዮሳፍጥ ሲል እንጂ ኢዮራምን እንደ ቁም ነገር እንደማይቆጥረው ከነበረው እርግጠኝነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ የመሐላ ያህል ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፊቱ የቆምሁት የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሕያው የመሆኑን ያህል ይህንንም በእርግጠኝነት ነው የምነግርህ››

በፊቱ የቆምሁት

እዚህ ላይ ያህዌን ማገልገል በፊቱ መቆም እንደ ሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የማገለግለው ያህዌ››

የይሁዳን ንጉሥ ኢዮፍጥን ባላከብር ኖሮ፣ አንተን አላይም ወይም ጉዳዬ አልልህም ነበር

ይህን በአዎንታዊ መልኩ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተን የማናግርህ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥን ስለማከብር ነው››

የኢዮሳፍጥን ፊት አከብራለሁ

እዚህ ላይ የኢዮሳፍጥ ፊት የእርሱን መገኘት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮሳፍጥን አከብራለሁ››

አንተን አላይም ወይም ጉዳዬ አልልህም ነበር

የእነዚህ ሁለት ሐረጐች ትርጒም ተመሳሳይ ሲሆን፣ ለኢዮራም ይህን ያህል ግምት እንደሌለው አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአንተ ጋር ምንም ዐይነት ጉዳይ የለኝም››