am_tn/2ki/03/11.md

1.7 KiB

በእርሱ አማካይነት ያህዌን ለመጠየቅ እንድንችል የያህዌ ነቢይ እዚህ የለምን?

ኢዮሳፍጥ እንዲህ በማለት የጠየቀው፣ እዚያ ነቢይ መኖሩንና እርሱን ፈልገው ማግኘት እንዳለባቸው ለማመልከት ነው፡፡ ይህን እንደ ዐረፍተ ነገር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚህ ቦታ የያህዌ ነቢይ እንደሚኖር እርግጠኛ ነኝ፤ በእርሱ አማካይነት ያህዌን እንድጠይቅ የት እንደማገኘው ንገሩኝ››

ሣፋጥ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

የኤልያስን እጅ ያስታጥብ የነበረው

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር የኤልያስ ረዳት ማለት ነው፡፡ ‹‹እጅ ማስታጠብ›› ኤልያስን ያገለግል የነበረበትን መንገድ የሚገልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኤልያስ ረዳት የነበረው››

የያህዌ ቃል ከእርሱ ዘንድ ይገኛል

ይህ ማለት ነቢይ ነበር፤ መናገር ያለበትን ያህዌ ይነግረው ነበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የነገረውን ይናገር ነበር››

ወደ እርሱ ወረዱ

ኤልሳዕን ለማየትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከእርሱ ለመጠየቅ ሄዱ፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኤልሳዕን ለማየትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመጠየቅ ወደ እርሱ ሄዱ፡፡››