am_tn/2ki/03/01.md

2.4 KiB
Raw Permalink Blame History

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት

ይህ የሚያመለክተው አሁን ያለው የይሁዳ ንጉሥ ምን ያህል ዓመት እንደ ገዛ በማሳየት ኢዮራም መንገሥ የጀመረበትን ጊዜ ነው፡፡ የዚህን ዐረፍተ ነገር ትርጒም በጣም ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢዮሳፍጥ የይሁዳ ንጉሥ በሆነ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት››

ዐሥራ ስምንተኛው ዓመት

18 ዓመት››

የአክአብ ልጅ ኢዮራም

አንዳንዴ ይህ ሰው ኢዮሮብዓም ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ይህ 2 ነገሥት 1፥17 ላይ ካለው ‹‹ኢዮራም›› የተለየ ነው፡፡

በያህዌ ፊት ክፉ የሆነውን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ፊት›› የያህዌን ሐሳብ ወይም አስተያየት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ክፉ ብሎ የሚያስበውን›› ወይም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ የሆነውን››

አባትና እናቱ እንደ ፈጸሙት ዐይነት አልነበረም

ይህ የሚያመለክተው ወላጆቹን ያህል ባይሆንም፣ እርሱም ብዙ ኀጢአት ማድረጉን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቱና እናቱ ያደረጉትን ያህል ክፉ ነገር አላደረገም፡፡››

የበአል ሐውልት

ምንም እንኳ ሐውልቱ ምን ዐይነት እንደ ነበር ባይታወቅም፣ በአልን ለማምለክ ጥቅም ላይ የሚውል ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአል የሚመለክበት ሐውልት››

በኀጢአት ተያዘ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ‹‹በኀጢአት ተያዘ›› ያንን ማድረግ ቀጠለ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአት ማድረጉን ቀጠለ››

ናባጥ

ይህ የሰው ስም ነው፡፡

ከዚያ ዘወር አላለም

ከአንድ ነገር፣ ‹‹ዘወር›› ማለት ያንን ማድረግ መተው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያንን ኀጢአት ማድረጉን አልተወም›› ወይም፣ ‹‹ያንን ኀጢአት ማድረግ ቀጠለ››