am_tn/2ki/02/05.md

1.2 KiB

በኢያሪኮ የነበሩትም የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ መጥተው እንዲህ አሉት፡፡

‹‹ኤልያስና ኤልሳዕ ወደ ኢያሪኮ ሲመጡ እዚያ የነበሩ የነቢያት ልጆች ኤልሳዕን እንዲህ አሉት››

የነቢያት ልጆች

እነዚህ በቀጥታ የነቢያት ልጆች ሳይሆኑ የነቢያት ስብስብ ናቸው፡፡ 2 ነገሥት 2፥3 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የነቢያት ስብስብ››

ሕያው ያህዌን በሕያው ነፍስህም እምላለሁ

‹‹ያህዌ ሕያው እንደ መሆኑ፣ አንተም ሕያው እንደ መሆንህ ከአንተ አልለይም›› እዚህ ላይ ኤልሳዕ የያህዌንና የኤልያስን ሕያውነት ከሚናገረው ነገር እርግጠኝነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ ቃል ኪዳን የሚደረግበት መንገድ ነው፡፡ 2 ነገሥት 2፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተገጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአንተ እንደማልለይ እምላለሁ››