am_tn/2ch/35/20.md

2.6 KiB

ቤተ መቅደሱን አሰናዳ

ይህ ማለት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረውን አምልኮ በማደስ እንደ እግዚአብሔር ኃሳብ እንዲሆን አድርጎታል ፡፡ ኣት: “የቤተመቅደሱን አምልኮ ወደ ተገቢው መንገድ መልሶታል” (የሚጠበቁ እውቀቶችን ወይም ያልተገለጹ መረጃዎችን ፡ይመልከቱ)

የግብፅ ንጉሥ ኒካዑ ወጣ

ይህ የግብፅ ንጉሥ ስም ነው ፡፡ እዚህ ንጉሡ ራሱን እና ሠራዊቱን ይወክላል ፡፡ ኣት: “የግብፅ ንጉሥ ኒካዑ ከሠራዊቱ ጋር ወጣ” ( የስሞች አተረጓጎምን እና ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱሰን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)

በከርከሚሽ ላይ

ይህ የከተማ ስም ነው ፡፡ እዚህ ከተማዋ የሚኖሩትን ሰዎች ትወክላለች ፡፡ ኣት: - “በከርከሚሽ ሰዎች ላይ” ( የስሞችን አተረጓጎም እና የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

ኢዮስያስ እርሱን ሊዋጋ ሄደ

እዚህ ሁለቱም ኢዮስያስ እና ኒካዑ ራሳቸውን እና የጀባቸውን ሠራዊቶቻቸውን ይወክላሉ ፡፡ ኣት: “ኢዮስያስና ሠራዊቱ ኒካዑ እና በሠራዊቱን ሊዋጉ ሄዱ” ( ሁሉን በአንዱ መወከልን ፡ይመልከቱ)

የይሁዳ ንጉሥ ሆይ ፣ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?

ኒካዑ ይህን አወያይ መጠይቅ ተጠቅሞ ለኢዮስያስ ከእሱ ጋር ግጭት እንደሌለው እና ኢዮስያስም እርሱን ማጥቃት እንደሌለበት ይነግረዋል፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል ፡፡ኣት፡ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ ፣ እኔን ለማጥቃት ምክንያት የለህም።” ( አወያይ መጠይቅን ፡ይመልከቱ)

በአንቺ ላይ አልመጣሁም

እዚህ ንጉሡ ኢዮስያስ መንግሥቱን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “የንተን መንግሥት እየተዋጋሁ አይደለም” ( ሁሉን በአንዱ መወከልን ፡ይመልከቱ)

ከቤቱ ጋር

እዚህ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የባቢሎንን ቤት ሲሆን “ቤት” ማለት መንግስቱን የሚወክል ነው ፡፡ መንግሥቱ የሚለው የባቢሎናውያንን ሰራዊት የሚያወሳ ዐውደ-ጽሑፍ ነው ፡፡ ኣት: - “ከባቢሎን ቤት ጋር ” (የባህሪ ስም እና ሁሉን በአንዱ መወከልን ፡ይመልከቱ)