am_tn/2ch/35/05.md

1.8 KiB

ቦታችሁን ይዛችሁ በቅዱሱ ስፍራው ቆሙ

“በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቦታችሁን ጠብቁ”

በክፍሎቻችሁ

ይህ ህዝቡ እያንዳንዱን ሌዋዊ የሾመበትን የሥራ ቡድንን ይመለከታል ፡፡ ይህንን በ 2 ኛ ዜና መዋዕል 35 ፡ 4 እንዴት እንደተረጉሙት ይመልከቱ ፡፡

የዘር ሐረግ ቤቶች

ይህ በሌዋውያን መካከል ያሉትን የተለያዩ ነገዶች ይመለከታል ፡፡ ለእያንዳንዱ ነገድ ወይም ቅድመ አያት ቤት በተሰየመው ዓይነት ሥራ መሠረት ሌዋውያን ለተለያዩ የሥራ ቡድኖች የተመደቡ ይመስላል ፡፡ ይህንን በ 2 ኛ ዜና 35፡4 እንዴት እንደተረጎምከ ተመልከት ፡፡

ራሳችሁን ቀድሱ

ይህ ምናልባት ካህናቱና ሌዋውያኑ በቤተመቅደሱ ውስጥ ከመሥራታቸው በፊት ራሳቸውን የሚያጥቡትን ሊያመለክት ይችላል።

በሙሴ እጅ እንደ ተሰጠው እንደ እግዚአብሔር ቃል ይደረግ ዘንድ

እዚህ “እጅ” የሚለው ቃል ራሱ ሙሴን ያመለክታል። ትዕዛዙን ለመስጠት እግዚአብሔር እንደ ወኪሉ ሙሴን ተጠቅሟል ፡፡ ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊተረጎም ይችላል። ኣት: - “እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለሕዝቡ የሰጣቸውን ትእዛዛት ሁሉ ለመታዘዝ” ወይም “እግዚአብሔር ሙሴን ለሕዝቡ እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ለመፈጸም” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን እና ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ )