2.0 KiB
2.0 KiB
እነሆ ፣ በእስራኤል ሥራዎች ... ተጽፈው ነበር
“ማንኛውም ሰው ሥራዎቹን ማየት ይችላል … እስራኤልን እዚያ እንደተጻፈ ማየት ይችላል”
ተጽፈዋል… ተጽፈውባቸዋል
እነዚህ ሐረጎች በገቢራዊ አረፍተነገሮች ሊገለጹ ይችላሉ። ኣት: - “ሰዎች ጻፏቸው … ሰዎች ስለእነርሱ ጻፉ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ)
የእስራኤል ነገሥታት ሥራ
ይህ በእስራኤል የታሪክ መዝገብ ውስጥ አሁን የማይገኝ ነው ፡፡
በኮረብታው ላይ የነበሩትን መስገጃዎች የሠራበት ፥ የማምለኪያ አጸዶችን እና የተቀረጹ ምስሎችን ያቆመበት ቦታ
ምናሴ ሕንጻውንና ግንባታውን አልሠራም ፣ ይልቅ ሠራተኞቹን እንዲሠሩ አዟል ፡፡ ኣት: - “የኮረብታው መስገጃዎች ያሠራበት ፣ እና የማምለኪያ አጸዶቹን እና የተቀረጹ ምስሎችን ያስቆመበት ሥፍራ ፤” ወይም “ሠራተኞቹን የኮረብታ መስገጃዎቹን እንዲገነቡና የማምለኪያ አጸዶቹን እና የተቀረጹ ምስሎችን እንዲያቆሙ ” (የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)
በባለ ራእዩ ታሪክ መጽሐፍ
ይህ የማይገኝ መጽሐፍ ነው።
ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ
ይህ አክብሮት ያለው አገላለጽ ነው። አት: - “ምናሴ ሞተ” ( ዘወርዋራን ፡ይመልከቱ)
በገዛ ቤቱ
“በቤተ መንግሥቱ”
አሞጽ
ይህ የሰው ስም ነው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)
በእርሱ ቦታ ነገሠ
ይህ ፈሊጥ ነው ፡፡ ኣት: - “ቀጣዩ ንጉሥ ሆነ” ወይም “የይሁዳ ንጉሥ ሆነ” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)