am_tn/2ch/30/25.md

3.2 KiB

የይሁዳ ጉባኤ ሁሉ

እዚህ ላይ “ይሁዳ” ምናልባት የደቡቡን የእስራኤል ነገዶች ያመለክታል ፡፡

ከእስራኤል የተሰበሰበ ሕዝብ ሁሉ

እዚህ “እስራኤል” የሚለው ምናልባት የሚያመለክተው ሰሜናዊያኑን የእስራኤል ነገዶች ነው ፡፡ ሰዎቹ የነዚያ ነገዶች አባላት ናቸው ፡፡ በይሁዳም ወደነበረው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ፡፡ ኣት: - “ከሰሜን እስራኤል በአንድነት የተሰበሰበ ሕዝብ ሁሉ” ( የሚጠበቁ እውቀት ካልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ከእስራኤል ምድር የመጡ የባዕድ አገር ሰዎች

እዚህ “የእስራኤል ምድር” የሚለው ምናልባት በሰሜናዊ የእስራኤል ነገዶች የተያዙትን መሬት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ፡፡ ኣት: “ከሰሜን እስራኤል ምድር የመጡት የባዕድ አገር ሰዎች” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

በይሁዳ የኖሩት

እዚህ“ይሁዳ” የሚለው ምናልባት በደቡባዊው የእስራኤል ነገዶች የተያዙትን መሬት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ፡፡ ኣት: - “በይሁዳ የኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች” ( የሚጠበቁ እውቀቶችን እና ያልተገለጹ መረጃዎችን ፡ይመልከቱ)

ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ዘመን ጀምሮ

“የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ ከነገሠበት ጊዜ አንስቶ” ወይም “የዳዊት ልጅ ሰሎሞን የእስራኤል ንጉሥ ንጉሥ ሳለ ህዝቡ ካከበሩት ከፋሲካ በዓል ጀምሮ”

በኢየሩሳሌምም እንደዚህ ያለ ነገር አልነበረም

“በኢየሩሳሌም በዚህ መልኩ የተከበረ የፋሲካ በዓል አልነበረም”

ድምፃቸው ተሰማ… ጸሎታቸውም እግዚአብሔር ወደሚኖርበት ወደ ቅድስት ሰማይ ወጣ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን የሚያመለክቱት እግዚአብሔር ለጸሎታቸው በጎ ምላሽ እንደሰጣ ነው ፡፡ ኣት: “እግዚአብሔር በሰማይ በተቀደሰ ማደሪያው ሆኖ ጸሎታቸው ሰማ በበጎም መለሰላቸው” ወይም “በቅዱሱ ሰማይ ውስጥ የሚኖር አምላክ ጸሎታቸውን ሰማ” ( ምስስልን ፡ይመልከቱ)

ድምፃቸው ተሰማ

ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: “እግዚአብሔር ድምፃቸውን ሰማ” ወይም “እግዚአብሔር የለመኑትን ሰማ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን፡ይመልከቱ)

ጸሎታቸው ወደ ሰማይ ወጣ

ጸሎታቸው ወደ ሰማይ መሄዱ በሰማይ ያለ እግዚአብሔር በምድር ላይ ለሚጸልዩ ለእነሱ ትኩረት እንደሚሰጥ የሚያመለክት ነው ፡፡ ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)