am_tn/2ch/30/21.md

1.5 KiB

የቂጣውን በዓል ጠበቀ

እዚህ “በዓሉን ጠበቁ” የሚለው ፈሊጥ በበዓሉ ላይ ተሳተፉ ወይም በዓሉን አከበሩ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኣት: - “በዓሉን አከበሩ” (ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

ታላቅ ድምጽ ባላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች ለእግዚአብሔር መዘመር

“ለእግዚአብሔር ከፍተኛ ድምጽ ያላቸውን የሙዚቃ መሣሪያዎች መጫወት እና መዘመር”

የእግዚአብሔርን አገልግሎት የተረዳ

ያበረታታቸውም ለዚህ ነበር ፡፡ ኣት: - “የእግዚአብሔርን አገልግሎት ስለተረዱ” ወይም “ያህዌን በብቃት ስላገለገሉ” (መለየትን ከማስታወቅና ከማስታዎስ ጋር ፡ይመልከቱ)

ስለዚህ እነርሱ በበዓሉ ላይ ሁሉ በሉ

“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው ፡፡

ለእግዚአብሔር እየተናዘዙ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እየተናዘዙ” የሚለው እዚህ ላይ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ታላቅ መሆኑን ማወጅን ነው ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔርን ማወደስ” ወይም 2) “መናዘዝ” እዚህ ላይ ኃጢአታቸውን መናዘዝን ያመለክታል። ኣት: - “ኃጢአታቸውን ወደ እግዚአብሔር መናዘዝ”