am_tn/2ch/30/18.md

2.6 KiB

ኤፍሬም ፣ ምናሴ ፣ ይሳኮር እና ዛብሎን

እነዚህ በሰሜናዊው የእስራኤል ክፍል ይኖሩ የነበሩ የአንዳንድ ነገዶች ስሞች ናቸው። በ 2ኛ ዜና 30 ፡10 ውስጥ “ዛቡሎን” የሚለውን እንዴት እንደተረጉምከው ተመልከት ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

የተጻፈውን ትዕዛዝ በመተላለፍ

መመሪያዎችን የሚቃወም ነገር ማድረግ ማለት ለመመሪያዎቹ ባለመታዘዝ አንድን ነገር ማድረግ ማለት ነው ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ መመሪያዎቹ ግልጽ ሊደረጉ ይችላሉ ፡፡ ኣት: - “ምንም እንኳን የተፃፉት መመሪያዎች መጀመሪያ ራሳቸውን እንዲያነጹ ቢናገሩም” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸን መረጃ ፡ይመልከቱ)

ቸሩ እግዚአብሔር

እዚህ “ቸር” የሚለው ቃል እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ለህዝቡ የ ሚያሳስብ ነው ፡፡ ኣት: - “ቸር የሆነው እግዚአብሔር” ( መለየትን ከማስታወቅ ወይም ከማስታወስ ጋር ፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን

እዚህ“ልቡን የሚያቀናው” የሚለው አንድን ነገር ለማከናወን ጽኑ ውሳኔ መኖርን የሚወክል ሲሆን ፣ “እግዚአብሔርን መፈለግ” የሚለው ደግሞ እርሱን ማወቅን ፣ ማምለክን እና መታዘዝን የሚያመለክት ነው ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ የወሰነ ማንኛውም ሰው” ወይም “በእውነት እግዚአብሔርን ለማክበር የሚፈልግ ሁሉ” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን ሰማው

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሕዝቅያስ በጎ ምላሽ እንደሰጠ ያሳያል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔርም ለሕዝቅያስ መልካም ምላሽ ሰጠው” ወይም “እግዚአብሔር ሕዝቅያስ የጠየቀውን አደረገ” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ሕዝቡን ፈወሰ

እዚህ “ህዝቡን ፈወሰ” የሚለው ሰዎችን ይቅር ለማለቱ እና እነርሱን የማይቀጣ ለመሆኑ ምልክት ነው ፡፡ ኣት: - “ህዝቡን ይቅር አለ” ወይም “ሕዝቡን አልቀጣም” ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)