2.3 KiB
የኤፍሬምና የምናሴ ክልሎች
ኤፍሬምና ምናሴ በእስራኤል ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ነገዶች ነበሩ። እዚህ ላይ “ኤፍሬም እና ምናሴ” የሚለው ሐረግ የሰሜናዊው እስራኤል አሥሩ ነገዶች አባላት የሆኑትን ሰዎች ሁሉ ያመለክታል፡፡ በ 2ኛ ዜና 30፡ 30 ውስጥ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ ኣት: - “የሰሜናዊ የእስራኤል ነገዶች ግዛቶች” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)
እስከ ዛብሎን ድረስ
ዛብሎን በእስራኤል ሰሜን ጫፍ ውስጥ ከሚገኙት ነገዶች መካከል አንዱ ነበር ፣ ነገር ግን ከእነርሱ አልፈው ወደ ሰሜን ጥግ የሚደርሱ ሌሎች ሦስት ነገዶች ነበሩ።
የእግዚአብሔርም እጅ በይሁዳ ላይ ወረደ
እዚህ“የእግዚአብሔር እጅ” የሚለው የእርሱን አመራር የሚወክል ሲሆን ልክ በእጁ እየመራቸው ያለ ይመስላል። አት:- “እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ መራ።” ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)
አንድ ልብ ለመስጠት
“አንድ ልብ” መኖሩ አንድነትን እና መስማማትን ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “እንዲስማሙ ማድረግ” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)
ትዕዛዙን እንዲያደርጉ
እዚህ “ትዕዛዙን ማድረግ” የሚለው አባባል የታዘዘውን ማድረግ የሚል ትርጉም አለው። ኣት: - “ትዕዛዙን መታዘዝ” (ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትዕዛዝ
“በእግዚአብሔር ቃል” የሚለው ሐረግ የሚያሳየው ንጉሡና መሪዎቹ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ትዕዛዙን እንደሰጡ ያሳያል ፡፡ ኣት: - “ንጉሡና መሪያዎቹ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ የሰጧቸው ትእዛዝ” ወይም “እግዚአብሔር ከተናገረው ነገር የተነሳ ንጉሡና መኳንንቱ ያዘዙት”