am_tn/2ch/30/07.md

3.7 KiB

አያያዥ መግለጫ

ይህ ለእስራኤል ሕዝብ የንጉሥ ሕዝቅያስ ቀጣይ መልእክት ነው ፡፡

ወንድሞችህ

እዚህ ላይ “ወንድሞችህ” ሌሎች የእስራኤል ሰዎችን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ሕዝብህ”( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ድንጋጤ አደረጋቸው

“ድንጋጤ” የሚለው ረቂቅ ስም በ “አስፈሪ” ወይም “አሰቃቂ” በሚሉት ቃላት ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ደራሲው እግዚአብሔር በአያቶቻቸው ላይ ስላደረገው ነገር ሲጽፍ ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ሲያዩ የሚሰማቸውን ስሜት በሚገልጽ ቋንቋ ጽፏል ፡፡ ኣት: - “ሰዎች ለማየት የሚፈሩት ነገር ነው ያደርጋቸው ” ( የረቂቅ ስሞችን እና የባህሪ ስምን፡ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር ራሳችሁን ስጡ

ይህ ለእግዚአብሔር መገዛትን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ለእግዚአብሔር ተገዙ” ወይም “ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ወደ ቅዱስ ስፍራውም ግቡ

“የተቀደሰ ስፍራ” የሚለው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ያመለክታል ፡፡ ኣት: “ ቅዱስ ነውና በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ ኑ”ወይም“ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደሱ ኑ ” ( የባህሪ ስምን፡ይመልከቱ)

ጹኑ ቁጣው ከእናንተ ይመለስ ዘንድ

ደራሲው ስለ ቁጣ ሲጽፍ ፣ እንደ ሰብአዊ አካል ከሰዎች የሚርቅ አስመስሎ ነው። የእግዚአብሔር ቁጣ ከእነሱ መመለሱ ከእንግዲህ በእነርሱ ላይ ቁጣው እንዳልቀጠለ ያሳያል ፡፡ ኣት: - “ከእንግዲህ በእናንተ ላይ እንዳይቆጣ” (ተስብኦትን ፡ይመልከቱ)

ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ

እዚህ “ወደ እግዚአብሔር ተመለስ” የሚለው እንደገና ለእርሱ መገዛትን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ለእግዚአብሔር እንደገና ብትሰጡ ” ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ ማርከው በሚወስዷቸው ፊት ምህረትን ያገኛሉ

እዚህ ላይ “ምህረትን ያገኛሉ” የሚለው ዘይቤአዊ አገላለጽ ሲሆን ምህረትን ይለማመዳሉ ማለት ነው ፡፡ እነርሱን “ማርከው በሚወስዷቸው ፊት .. ያገኛሉ” የሚለው ማርከው የሚወስዷቸው ምህረትን ያሳየዋቸዋል ማለት ነው፡፡ ኣት: - “ወንድሞችህና ልጆችህ በግዞት ከወሰዷቸው ሰዎች ርኅራሆ ያገኛሉ” ወይም “ወንድሞችህንና ሕፃናትን ግዞተኛ አድርገው የወሰዷቸው ሰዎች ርኅራሄ ያሳዮአቸዋል” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ፊቱን ከአንተ አይርቅም

እዚህ “ፊቱን ከእናንተ ማራቅ” የሚለው አባባል እነርሱን አለመቀበልንና እነርሱን ለመጠበቅ ፈቃደኛ አለመሆንን ያሳያል። ኣት: - “አይጥልህም”( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ወደ እርሱ ብትመለሱ

እዚህ “ወደ እርሱ ተመለስ” የሚለው ለእግዚአብሔር መገዛትን ያሳያል ፡፡ ኣት: - “እንደገና ለእርሱ ብትገዙ” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)