am_tn/2ch/30/04.md

1.4 KiB

ይህ ሀሳብ

ይህ ፋሲካን በመጀመሪያው ወር ፋንታ በሁለተኛው ወር ለማክበር የቀረበለትን ሀሳብ ያመለክታል ፡፡

በንጉሡና በጉባኤው ሁሉ ፊት

ዐይን ማየትን የሚወክል ሲሆን ማየት ደግሞ አመለካከትን ወይም ውሳኔን ይወክላል። ኣት: - “በንጉሡና በጉባኤው ሁሉ እይታ” ወይም “ለንጉሡና ለማኅበሩ ሁሉ” ( ዘይቤያዊን፡ይመልከቱ)

ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ

እነዚህ የእስራኤል ደቡባዊ ጫፍ እና ሰሜናዊ ጫፍ ናቸው ፡፡ ጸሐፊው በዚህ መንገድ በመጥቀስ እስራኤል ሁሉ የተካተተ መሆኑን ጎላ አድርጎ አመልክቷል ፡፡ ኣት: - “በደቡብ በኩል ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ሰሜን ዳን ድረስ” (ፈሊጥ ፡ይመልከቱ)

እንደ ተጻፈ

“እንዲያደርጉት ተብሎ እንደተጻፈ።” ብዙ ሕዝብ ሆነው ፋሲካን ማክበር እንዳለባቸው መፃፉን ተጠቁሟል ፡፡ ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ሙሴ እንዲጠብቁት እንደጻፈው” ( የሚጠበቅ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ ፡ይመልከቱ)