am_tn/2ch/29/15.md

3.3 KiB

የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል

ይህ ሐረግ ንጉሡ የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ ተዕዛዝ እንደሰጠ ያሳያል ፡፡ ኣት: - “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ” ወይም “እግዚአብሔር ስለተናገረ”

የእግዚአብሔርን ቤት ያነጻ ዘንድ

ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተስማሚ ስለሆን ቦታ በአካል ንፁህ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል ፡፡ (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቤት ... የቤቱ አደባባይ

እዚህ “ቤት” የሚለው ቃል ቤተመቅደሱን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ…...የቤተ መቅደሱ አደባባይ (የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር መቅደስ ያገኙትን እርኩስ ነገር ሁሉ አወጡ

“ርኩስ” የሚለው ቃል ህዝቡ ሌሎች አማልክትን ለማምለክ ይጠቀሟቸው የነበሩትን እቃዎች የመለከታል ፡፡ ተራኪው ስለ እነዚህ ሲናገር ቤተመቅደሱን አንዳቆሸሹት እና ለእግዚአብሔር ተገቢ እንዳይሆን እንዳደረጉት ይናገራል ፡፡ ኣት: “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያገኙትን ርኩስ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አወጡ” ወይም “ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር ተስማሚ እንዳይሆን ያደረጉትን ነገሮች ሁሉ አወጡ” ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ቄድሮን ወንዝ

ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚፈስ ትንሽ የውሃ አካል ነው። አንዳንድ ጊዜ እንደ ቆሻሻ መጣያ ያገለግላል፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን

ይህ የዕብራይስጥ የቀን አቆጣጠር የመጀመሪያ ወር ነው። የመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ያወጣበት ቀን ነው። ይህ በምዕራባዊያን የቀን መቁጠሪያ ላይ በመጋቢት አጋማሽ አካባቢ ነው። ( የዕብራዊያን ወራት እና ሕገኛ ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

በዚያም ወር በስምንተኛው ቀን

ይህ በምዕራባዊያን የቀን መቁጠሪያዎች ላይ በመጋቢት መጨረሻ አካባቢ ነው። ( የዕብራዊያን ወራትን እና ሕገኛ ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

ወደ እግዚአብሔር ቤት ወለል ደረሱ

“የእግዚአብሔር ቤት ወለል” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የቤተ መቅደሱን በረንዳ ነው። “ደረሱ” ማለት ይህንን ክፍል ማጽዳት ጀመሩ ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በረንዳ ማንጻት ጀምረው ነበር” ( የባህሪ ስምን እና ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

በመጀመሪያው ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን

ይህ በምእራባዊያን የቀን መቁጠሪያዎች ላይ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ አካባቢ ነው። ( የዕብራዊያን ወራትን እና ሕገኛ ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)