am_tn/2ch/29/03.md

2.0 KiB

በመጀመሪያው ወር

ይህ በዕብራይስጥ የቀን አቆጣጠር የመጀመሪያ ወር ነው። እንደ ምዕራባዊያን የቀን አቆጣጠር ወቅቱ የመጋቢት የመጨረሻ ክፍል እና የሚያዚያ የመጀመሪያ ክፍል ነው። ( የዕብራዊያንን ወራት እና ሕገኛ ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቤት

እዚህ “ቤት” የሚለው ቃል ቤተመቅደሱን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ያእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” ( የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

ሕዝቅያስ በሮቹን ከፈታቸው አደሳቸውም

ሕዝቅያስ ንጉሥ ስለነበረ ሠራተኞቹ እነዚህን ነገሮች እንዲሠሩ አድርጎ ይሆናል። ኣት: “ሕዝቅያስ ሠራተኞቹን በሮቹን እንዲከፍቱ እና እንዲጠግኗቸው አዘዘ” ( የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

በምሥራቅ በኩል

ይህ የቤተ መቅደሱን ምስራቅ ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “በቤተ መቅደሱ በስተ ምሥራቅ” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ርኩሱን ነገር ሁሉ ከቅዱሱ ቦታ አስወግዱ

“ርኩሰት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ህዝቡ ሌሎች አማልክትን ሲያመልኩ የጠቀሙባቸውን የነበሩትን ነገሮች ነው ፡፡ ተራኪው ስለ እነዚህ ነገሮች ሲናገር መቅደሱ ከመቆሸሹ የተነሳ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ይናገራል፡፡ ኣት: - “የተቀደሰውን ሥፍራ የሚያረክሱትን ነገሮችን አስወግዱ” ወይም “የተቀደሰው ስፍራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ የሚያደርጉትን ነገሮች አስወግዱ” ( ዘይቤያዊን፡ይመልከቱ)