am_tn/2ch/28/22.md

1.4 KiB

በመከራው ጊዜ

“መከራ ሲደርስበት”

የደማስቆ አማልክት

እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም እንደሚያድር ሁሉ፣ ሶርያውያን ደማስቆ የአማልክቶቻቸው መኖሪያ ከተማ እንደ ሆነች ያምናሉ። ኣት: - “ሶርያውያን በደማስቆ ያሚያመልኳቸው አማልክት” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ያሸነፉጽ አማልክት

ይህ የአካዝን ሀሳብ ያሳያል ፡፡ ሶርያውያን እርሱ እና ሠራዊቱን ስላሸነፉ አካዝ ሽንፈቱን ሶርያውያን ለሚያመልኳቸው አማልክት ሰጥቷል ፡፡ ኣት: “የሶርያ ሠራዊት የሚያመልኳቸው አማልክት እርሱን እንዲያሸንፉ አስችለዋል” (የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

እነርሱ ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ጥፋት ነበሩ

“ጥፋት” የሚለው ቃል በግስ ሊተረጎም ይችላል። ኣት: - “እነዚያ አማልክት እርሱንም ሆነ እስራኤልን ሁሉ አወደሙ” (የረቂቅ ስሞችን ፡ይመልከቱ)

እስራኤል ሁሉ

እዚህ ላይ “እስራኤል” ደቡባዊውን የይሁዳን መንግሥት ይወክላል ፡፡