am_tn/2ch/28/12.md

1.6 KiB

፤ ዮሓናን ልጅ ዓዛርያስ ፥ የምሺሌሞት ልጅ በራክያ ፤ የሰሎምም ልጅ ይሒዝቅያ እና የሓድላይ ልጅ ዓሜሳይ።

እነዚህ ሁሉ የወንዶች ስሞች ናቸው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

ከጦርነት በተመለሱት ላይ ተነሱባቸው

“ተነሱባቸው” የሚለው ሐረግ መቃወምን ወይም ፊት ለፊት መጋፈጥን የሚገልጽ ፈሊጥ ነው ፡፡ ኣት: - “ከጦርነት የተመለሱትን መጋፈጥ” ወይም “ከጦርነት የተመለሱትን መቃወም” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

ኃጢአት በእኛ ላይ የሚያመጣ ነገር ነው

መሪዎቹ እነርሱን ጭምር ጥፋተኛ እና ኃጢአተኛ የሚያደርጋቸውን ተግባር ስለመፈጸማቸው ሲናገሩ ኃጢአት እንደ አንድ ቁስ በላያቸው ላይ እንደሚመጣ ይናገራሉ ፡፡ ኣት: - “ኃጢአተኛ እና በደለኛ የሚያደርገን ነገር ” ተመልከት ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

በእስራኤል ላይ አስፈሪ ቁጣ ሆነ

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር አስፈሪ ቁጣ በእስራኤል ላይ መሆኑን ነው ፡፡ “አስፈሪ ቁጣ ” የሚሉት ቃላት በቃል ሐረግ ሊተረጎሙ ይችላሉ ፡፡ አት: - “እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ እጅግ ተቆጣ” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና የልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)