am_tn/2ch/28/09.md

2.3 KiB

ዖዴድ

ይህ የሰው ስም ነው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው

እዚህ “እጅ” የሚለው ቃል ኃይልን ይወክላል ፡፡ የእስራኤልን ሠራዊት የይሁዳን ሠራዊት ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ስለማስቻሉ እግዚአብሔር የይሁዳን ሠራዊት በእስራኤል ሰራዊት እጅ እንዳስገኘ ተደርጎ ተገልጻል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር እንድታሸንፋቸው አስቻለህ” ( የባህሪ ስምን እና ዘይቤያዊን፡ይመልከቱ)

ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው፡፡

የእስራኤል ሠራዊት የይሁዳን ሠራዊት የገደለበት ቁጣ እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሷል ሲል ዖዴድ ስለ እግዚአብሔር ይናገራል ፡፡ ያደረጉትን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያውቅ ያውቃል እርሱም ምላሽ ይሰጣል ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር ራሱ አይቶ ይበቀላችሁ ዘንድ በታላቅ ቁጣ ገደላችኋቸው” ( ዘይቤያዊን እና የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ነገር ግን አምላካችሁን እግዚአብሔርን የበደላችሁት በደል በእናንተ ዘንድ የለምን?

ዖዴድ የእስራኤልን ሰራዊት ለመገሠጽ እና ጥያቄው የሚጠብቀውን አዎንታዊ መልስ ለማጉላት ይህንን አወያይ መጠይቅ ይጠይቃል ፡፡ ኣት: - “ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ በሠራችሁት ኃጢአት ጥፋተኞች ናችሁ።” ( አወያይ መጠይቅን ፡ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቁጣ በእናንተ ላይ ነድዶአል

ዖዴድ ስለእግዚአብሔር ከባድ ቁጣ ሲናገር ቁጣው ልክ እንደ አንድ ቁስ በላያቸው ላይ እንደ ሆነ አስመስሎ ተናግሯል፡፡ ኣት: - “በአንተ ላይ እግዚአብሔር እጅግ ተቆጥቷል” ( ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)