am_tn/2ch/28/05.md

3.2 KiB
Raw Permalink Blame History

የአካዝ አምላክ እግዚአብሔር በሶሪያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው

እዚህ “እጅ” የሚለው ዘይቤ ኃይልን ይወክላል። የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አካዝንና ሠራዊቱን እንዲያሸንፉ እግዚአብሔር አካዝን በሶርያ ንጉሥ እጅ እንዳስገባው ተደርጎ ተገልጾአል ፡፡ ኣት: - “የአካዝ አምላክ እግዚአብሔር የአራም ንጉሥ አካዝን እንዲያሸንፍ አስቻለው” ( የባህሪ ስምን እና ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ከእርሱ ወሰዱ

እዚህ ላይ “እርሱ” የአካንን ሰራዊት ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ከአካዝ ሰራዊት ተወሰደ ” ( የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

አካዝ እርሱን ድል ባደረገው በእስራኤል ንጉሥ እጅ ታልፎ ተሰጠ

እዚህ “እጅ” የሚለው ዘይቤ ኃይልን ይወክላል። እግዚአብሔር የእስራኤል ንጉሥ እና ሠራዊት አካዝንና ሠራዊቱን እንዲያሸንፍ ስለማስቻሉ እግዚአብሔር አካዝን በእስራኤል ንጉሥ እጅ እንዳስቀመጠው ተደርጎ ተገልጾአል ፡፡ ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: “እግዚአብሔርም የእስራኤል ንጉሥ አካዝን እንዲያሸንፍ አስችሎታል” (የባህሪ ስምን፣ ዘይቤያዊን፣ ገቢራዊን እና ተብሮኣዊን ፡ይመልከቱ)

የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ

ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነበር ፡፡ ሁለቱም ‹ፋቁሔ› እና ›ሮሜልዩ› የሰዎች ስሞች ናቸው ፡፡ (የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

120,000 ወታደሮች

“አንድ መቶ ሀያ ሺህ ወታደሮች” ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

ዝክሪ… መዕሤያን… ዓዝሪቃም … ሕልቃና

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

ኃያል ሰው

ይህ ጀግናን የሚያመላክት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው ፡፡ ኣት: - “ኃያል ተዋጊ” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

ከንጉሡ ቀጥሎ የነበረው

ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ይህ ሰው የንጉሡ ረዳት ነበር ማለት ሲሆን ከንጉሱ ቀጥሎ ስልጣን ያለው ሰው ነው፡፡ ኣት: - “በማዕረግ ከንጉሡ ቀጥሎ ነበር” ( ፈሊጥን፡ይመልከቱ)

የእስራኤል ጦር ከዘመዶቻቸው ምርኮኛ ወሰደ

“ከወገኖቻቸውም መካከል የእስራኤል ሠራዊት ምርኮኛ ወስደዋል።” “የእነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሠራዊት ነው ፡፡ ተራኪው የይሁዳ ህዝብ የእስራኤል ሰዎች ዘመዶች እንደሆኑ ይናገራል ፡፡

200,000 ሚስቶች ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆች

“ሁለት መቶ ሺህ ሚስቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆች” ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)