am_tn/2ch/28/03.md

1.6 KiB

የቤን ሄኖም ሸለቆ

ይህ በኢየሩሳሌም ያለ ሸለቆ ነው። ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

በእስራኤል ልጆች ፊት

እስራኤላውያን ወደ ምድሩ ሲገቡ የተሰደዱት የነዚያ አገራት ሕዝቦች ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልፅ ሊደረግ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ከእስራኤል ሕዝብ ቀድመው ወደ ምድሪቱ የገቡት” ወይም “የእስራኤል ሰዎች ወደ ምድሩ ሲጓዙ” (የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

በኮረብቶች ላይ ባሉት መስገጃዎች ፣ በኮረብቶች ላይና በእያንዳንዱ አረንጓዴ ዛፍ ሥር

እነዚህ የሌሎች አገራት ሕዝቦች የሐሰት አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸው ቦታዎች ናቸው።

በእያንዳንዱ አረንጓዴ ዛፍ ሥር

እግዚአብሔር ህዝቡ በኢየሩሳሌም ቅዱስ መስዋዕትን እንዲያቀርቡ ይፈልግ ነበር ፡፡ እዚህ “እያንዳንዱ” የሚለው ቃል ግነት ሲሆን ንጉሥ አካዝ በምትኩ በሌሎች ቦታዎች መስዋዕቶችን በማቅረብ እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ምን ያህል ቆርጦ እንደነበረ የሚያሳይ ነው ፡፡ ኣት: - “በብዙ አረንጓዴ ዛፎች ዙሪያ ” ወይም “በአገሪቱ ባሉ ብዙ አረንጓዴ ዛፎች ሥር” ( ግነትን እና አጠቃላይን ፡ይመልከቱ)