am_tn/2ch/27/05.md

2.2 KiB

እንዲሁም ከአሞን ህዝብ ንጉሥ ጋር ተዋጋ

ኢዮአታም ሠራዊቱን ወደ ውጊያ እንደመራ አንባቢው እንዲረዳው አድርጎ መተርጎም ሊኖርብህ ይችላል ፡፡ ኣት: “እርሱ ሠራዊቱን ከአሞን ሕዝብ ንጉሥ ጋር እንዲዎጋ መራ” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)

ከአሞን ህዝብ ንጉሥ ጋር

የአሞን ንጉሥ ሰራዊቱን ወደ ጌት እንደመራ አንባቢው እንዲረዳው መተርጎም የኖርብህ ይሆናል። ኣት: - “ከአሞን ንጉሥና ከሠራዊቱ ጋር” ( ሁሉን በአንሱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)

አንድ መቶ መክሊት ብር

ይህንን ወደ ዘመናዊ ልኬት መለወጥ ትችላለህ። “መክሊት” ከ 33 ኪሎግራም ጋር እኩል ነው ፡፡ ኣት: - “100 መክሊት ብር” ወይም “3,300 ኪሎ ግራም ብር” ( መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክብደትን እና ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

አሥር ሺህ መስፈሪያ ስንዴ

ይህንን ወደ ዘመናዊ ልኬት መለወጥ ትችላለህ። እዚህ “መስፈሪያ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል “ኮር” ሲሆን እና ከ 220 ሊትር ጋር እኩል ነው ፡፡ ኣት: - “10,000 መስፈሪያ ስንዴ ” ወይም “2,200 ኪሎ ግራም ስንዴ” ( የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘትን እና ቁጥሮችን፡ይመልከቱ)

አሥር ሺህ መስፈሪያ ገብስ

ይህንን ወደ ዘመናዊ ልኬት መለወጥ ትችላለህ ። እዚህ “መስፈሪያ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል “ኮር” ሲሆን ከ 220 ሊትር ጋር እኩል ነው ፡፡ አት: - “10,000 መስፈሪያ ገብስ” ወይም “2,200 ኪሎ ሊትር ገብስ” ( መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘትን እና ቁጥሮችን፡ይመልከቱ)

በሁለተኛው እና በሦስተኛው ዓመት ውስጥ

“እነርሱን ባሸነፈ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት”