am_tn/2ch/26/01.md

1.5 KiB

የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የአሥራ ስድስት ዓመት ልጅ የነበረውን ዖዝያንን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ፋንታ አነገሡት።

“ሁሉም” የሚለው ቃል ጠቅለል ያለ አገላለጽ ነው ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እርሱ ንጉሥ እንዲሆን አይፈልጉ ይሆናል ፡፡ ኣት: “የይሁዳ ሕዝብ የ 16 ዓመቱን ዖዝያንን ወስዶ በአባቱ በአሜስያስ ፋንታ አነገሡት” ( ግነትን እና አጠቃላይን ፡ይመልከቱ)

አስራ ስድስት…ሃምሳ ሁለት

“16… 52” ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

ኤላትን የሠራው እርሱ ነበር

ዖዝያን ብቻውን አሠራውም። ኣት: - “ኤላት እንደገና እንድትሠራ ያዘዘው እርሱ ነበር” ወይም “ኤላት እንደገና የተሠራው በእርሱ ቁጥጥር ነበር” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)

ኤላት

በይሁዳ ያለች ከተማ ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

ወደ ይሁዳ መለሳት

ወደ ይሁዳ መለሰው። ”ይህ ማለት የእርሱ ሠራዊት ከተማዋን ስለተቆጣጠረ እንደገና የይሁዳ ሆነች ፡፡

ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

ይህ መሞቱ የሚነገርበት መንገድ ነው ፡፡ ( ዘወርዋራ አነጋገርን ፡ይመልከቱ)