am_tn/2ch/25/18.md

1.7 KiB

በሊባኖስ የነበረው ኩርንችት… ኩርንችቱን ረገጠ

ይህ መልእክት ምሳሌያዊ መልክ ያለው ነው ፡፡ ከንቱ ኩርንችት አሜስያንን ይወክላል ፣ የሊባኖስ ዝግባው ደግሞ ኢዮስያስን ይወክላል።ኩርንችቱ በአውሬው መረገጡ መጥፎ ነገር እንደሚከሰትበት እና ይህን ለማስቆም ኃይል የሌለው መሆኑን ይገልጻል ፡፡ የምሳሌው ነጥብ አሜስያስ ኢዮአስን መገዳደር ሞኝነት መሆኑ ነው ፡፡ (ምሳሌን ፡ይመልከቱ)

ኩርንችት

ይህ ትንሽ ፣ ሹል እሾህ ያለው ተራ ተክል ነው።

ዝግባ

በጣም ትልቅ የዛፍ ዓይነት

ልብህ ከፍ ከፍ አደረገህ

ይህ ማለት ኩራተኛ ነው ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “ኩራተኛ ሆነሃል” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

አንተ ከይሁዳ ጋር ትወድቅ ዘንድ ስለምን መከራ ትሻለህ?

ኢዮስያስ አሜስያስን ከእርሱ ጋር እንዳይዋጋ ለማስጠንቀቅ ይህን አወያይ መጠይቅ ተጠቅሟል ፡፡ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ኣት: - “አንተ ከይሁዳ ጋር ሁላችሁንም ችግር ላይ መጣል የለብህም።” ( አወያይ መጠይቅን ፡ይመልከቱ)

መውደቅ

እዚህ “መውደቅ” “መሞት” ማለት ነው ፡፡

ይሁዳ

እዚህ ላይ “ይሁዳ” በይሁዳ የሚኖሩትን ህዝብ የተካ ስም ነው ፡፡ አት: - “የይሁዳ ሰዎች” ( ዘወርዋራን፡ይመልከቱ)