am_tn/2ch/23/14.md

2.2 KiB

ዮዳሄ

በ 2 ኛ ዜና 22 ፡11 እንዳለው የዚህን ሰው ስም ተርጉም ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

የመቶዎች አዛዦች

“የመቶዎች አዛዥ” የሚለው ሐረግ ምናልባት ወታደራዊ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “መቶዎች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እነዚህ አዛዦች የሚመሩትን ወታደሮች ትክክለኛ ብዛት ነው። ኣት: - “የ 100 ወታደሮች አዛዦች ” ወይም 2) “መቶዎች” ተብሎ የተተረጎመው ቃል የሚያመለክተው ትክክለኛውን ቁጥር ሳይሆን ወታደራዊ ክፍልን ነው። በ 2 ኛ ዜና 23 ፡1 ውስጥ እንዴት እንደተረጉምከው ተመልከት ፡፡ ኣት: - “የወታደር አዛዦች” ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

እነርሱ በሠራዊቱ ላይ ነበሩ

“በሠራዊቱ ውስጥ መሪ የነበሩት”

በደሰልፉ መካከል አውጧት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ከባችሁ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ አውጧት” ወይም 2) “በቤተመቅደሱ ግቢ ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አስወግዷት”

እርሷን የሚከተል ሁሉ በሰይፍ ይገደል

ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ እርሷን የሚከተሉ ሰዎች ሊረዷት እየሞከሩ ነው ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “እርሷን ለመርዳት የሚመጣውን ማንኛውንም ሰው ለመግደል ሰይፍህን ተጠቀም” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን እና የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ካህኑ እንዲህ ብሏል

“ካህኑ ዮዳሄ እንዲህ ብሏል”

ወደ ንጉሥ ቤት ወደ ፈረስ በር ገባች

አንዳንድ ትርጉሞች “ በነገሥታት ቤት መግቢያ አጠገብ ወዳለው የፈረስ በር ወሰዷት” የሚል አላቸው ፡፡

የንጉሥ ቤት

“ንጉሣዊው ቤተ መንግሥት”