am_tn/2ch/23/01.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በምዕራፍ 23 ውስጥ ሁሉ ፣ ኢዮአስ “ንጉስ” ተብሎ ተጠርቷል ፡፡ አልፎ አልፎ ማንነቱን ለአንባቢዎች በትክክል ለማሳየት “ንጉሥ ዮአስ” ወይም “ንጉሱ ኢዮአስ” ተብሎ ቢጻፍ ጥሩ ሊሆን ይችላል ፡፡ ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ዮዳሄ

በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግልና ለእግዚአብሔር የታመነ ሊቀ ካህን ነው። የኢዮአስ አማካሪ ነበር። (የስሞች አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

ጥንካሬውን አሳይቷል

የጎቶሊያን አገዛዝ ለመቃወም ጊዜው እንደሆነ ወስኖ ኢዮአስ በሕይወት መኖሩን እና ንጉሥ ለመሆን ዝግጁ መሆኑን ገለጸ ፡፡ አት: - “እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ”

የመቶዎች አዛዦች

“የመቶዎች አዛዦች” የሚለው ሐረግ ምናልባት ወታደራዊ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “መቶዎች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እነዚህ አለቆች የሚመሩትን ወታደሮች ትክክለኛ መጠን ነው። ኣት: - “የ 100 ወታደሮች አዛዦች” ወይም 2) “መቶዎች” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ወታደራዊ ክፍልን እንጂ ትክክለኛውን ቁጥር አይወክልም ።ኣት: - “የወታደራዊ ክፍል አዛዦች” ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)

ወደ ቃል ኪዳኑ ገባ

“ስምምነት አደረገ”

አዛርያስ… ይስማኤልን… ዓዛርያስ… መዕሤያ… ኤሊሳፋጥ

እነዚህ ሰዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አዛዦች ነበሩ። ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

ይሮሓም… ይሆሓናን… ዖቤድ… ዓዳያ… ዝክሪ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

የእስራኤል አባቶች ቤቶች ራሶች

እዚህ “ራሶች” በጣም አስፈላጊ የሆነ አካል ምሳሌ ነው ፡፡ “ቤቶች” ቤተሰቦችን ይወክላሉ ፡፡ ኣት: - “የእስራኤል መሥራች ቤተሰቦች መሪዎች” ( ዘይቤያዊን እና የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

የንጉሥ ልጅ

እዚህ “ንጉሥ” የሚለው የኢዮአስ አባትን ያመለክታል ፡፡ “የንጉሥ ልጅ ዮአስ”