am_tn/2ch/21/18.md

1.6 KiB

እግዚአብሔርም በማይድን በሽታ አንጀቱን መታው

እዚህ “መታው” የሚለው አባባል እግዚአብሔር እንዲታመም ያደረገው ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔርም የአንጀት ውስጥ የማይድን በሽታ እንዲሠቃይ አደረገው” ( ፈሊጥን፡ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ አንድን አስፈላጊ ሁኔታን ያሳያል ፡፡ ቋንቋህ ይህንን የሚያደርግበት መንገድ ካለው እዚህ መጠቀም ትችላለህ፡፡

በጊዜው

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ የተቀጠረን ወይም የተወሰነን ጊዜ የሚያመለክት። ኣት: - “በተገቢው ጊዜ” ወይም “በትክክለኛው ጊዜ” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

ለአባቶቹ እንዳደረጉት ሁሉ ለእርሱ እሳትን በማንደድ ክብር አልሰጠም

በእስራኤል ልማድ የሞተውን ንጉሥ ለማክበር አጥንት ያነዱ ነበር ፡፡ ለእርሱ ያላቸውን ንቀት ለመግለጽ ለኢዮራም ይህን አላደረጉለትም ፡፡ ይህ በግልጽ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “በተለምዶ ነገሥታት ሲሞቱ እንደሚያከብሩ ሁሉ ሊያከብሩት ቃል አልገቡም” ( የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)

ሲሄድ አንድ ሰው አላለቀሰለትም ነበር

“በመሞቱ ማንም አላዘነም”