am_tn/2ch/19/01.md

3.1 KiB

ባለ ራእዩ አናኒ

“አናኒ” የአንድ ሰው ስም ነው። በ 2 ኛ ዜና መዋዕል 16፡ 7 ውስጥ ይህንን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ (የስሞች አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

ሊገናኘው ወጣ

እዚህ ላይ “እሱ” የሚለው ቃል ኢዮሣፍጥን ያመለክታል ፡፡

ክፉዎችን መርዳት አለብህን? እግዚአብሔርን የሚጠሉትን መውደድ አለብህ?

እነዚህ ጥያቄዎች ኢዮሣፍጥ አክዓብን መርዳት አልነበረበትም የሚለውን ነጥብ ለማሳየት አሉታዊ መልሶችን ይጠብቃሉ ፡፡ ኣት: - “ክፉዎችን መርዳት የለብህም! ያህዌን የሚጠሉትን መውደድ የለብህም! ” (አወያይ መጠይቅን ፡ይመልከቱ)

ክፉዎች

ይህ በአጠቃላይ ክፉ ሰዎችን ያመለክታል። ኣት: “ክፉ ሰዎች” ( ስማዊ ቅጽልን ፡ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችሁ ነው

“ቁጣ” የሚለው እረቂቅ ስም “ተቆጣ” ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ይህ ሐረግ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር በአንተ ላይ ተቆጥቷል” ( የረቂቅ ስሞችን እና ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ )

በአንተ ውስጥ አንዳንድ መልካም ነገር አለ

ረቂቅ ስም የሆነው “ጥሩ” የሚለው ቃል እንደ ቅፅል ሊተረጎም ይችላል። ይህ ሐረግ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “አንዳንድ ጥሩ ነገሮችን አድርገሃል” ( የረቂቅ ስሞችን እና ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ)

የማምለኪያ ዐፀዶቹን ከምድሩ አስወግደሃል

ኢዮሣፍጥ ንጉሥ ስለነበረ ፣ እነዚህን ነገሮች እንዲያደርጉ ለሠራተኞቹ ነግሮ ሊሆን ይችላል። ኣት: - “ሕዝብህ የማምለኪያ ዐፀዶችን ከምድሪቱ እንዲወስወግዱ አድርገሃቸዋል” ( የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)

የማምለኪያ ዐፀዶች

ይህንን በ 2 ኛ ዜና ምዕራፍ 14 ፡3 እንዴት እንደጸሮጎምከው ተመልከት ፡፡

ልብህን አዘጋጅተሃል

እዚህ ልብ ፈቃዱን ይወክላል ፡፡ የኢዮሳፍጥ ፈቃድ እንደ ማይለወጥ ወይም የማይነቃነቅ ነው ተብሎ ተነግሯል ፣ ይህም ማለት እግዚአብሔርን የመሻት የማይለወጥ አቋም አለው ፡፡ ኣት: - “በጥብቅ ወስኗል” ( ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ፈልግ

ኢዮሣፍጥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ለማድረግ መፈለጉ እርሱን እየፈለገ እንዳለ ተደርጎ ተነግሯል። ኣት: - “እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን አድርግ” ( የባህሪ ስምን ፡ይመልከቱ)