am_tn/2ch/15/08.md

2.4 KiB

አሳ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ፣ የነቢዩን የዖዴድ ትንቢት

“አሳ ነብዩ ዖዴድ የተናገራቸውን ቃላት ሰማ” ወይም “አሳ የዖዴድ ትንቢት በሚሰማበት ጊዜ።” “የነቢዩ የዖዴድ ትንቢት” የሚለው ሀረግ “እነዚህ ቃላት” ይገልጻሉ ፡፡

የነቢዩ ዖዴድ ትንቢት

UDBን ጨምሮ ብዙ ትርጉሞች ይህንን ክፍል “የነቢዩ የኦዴድ ልጅ የአዛርያስ ትንቢት” እንዲነበብ ያደርጉታል ፡፡ ይህን የሚያደርጉት በ 2ኛ ዜና መዋዕል 15: 1 ካለው ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ነው ፡፡ ተርጓሚዎች በሕትመታቸው ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይፈልጉ ይሆናል።

የነቢዩ ዖዴድ ትንቢት

UDBን ጨምሮ ብዙ ትርጉሞች ይህንን ክፍል “የነቢዩ የኦዴድ ልጅ የአዛርያስ ትንቢት” እንዲነበብ ያደርጉታል ፡፡ ይህን የሚያደርጉት በ 2ኛ ዜና መዋዕል 15: 1 ካለው ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ነው ፡፡ ተርጓሚዎች በሕትመታቸው ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይፈልጉ ይሆናል።

አስጸያፊ ነገሮችን አስወገደ

“አስጸያፊ ነገሮች” የሚሉት ቃላት ጣዖታትን ያመለክታሉ። ህዝቡ ጣዖታቱን እንዲያወድም ወይም እንዲያጠፋ ማድረግ እነርሱን ጠራርጎ ማስወጣት እንደሆነ ተደርጎ ተገልጻል ፡፡ ኣት: - “አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖታት አስወገዱ” (የሚጠበቅ እውቀትን እና የልተገለጸ መረጃን እና ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)

ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ ሰበሰበ

እዚህ ላይ “ሁሉም” የሚለው ቃል አጠቃላይ ነው ፡፡ የሐረጉ ትርጉም ዳዊት መላውን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሰበሰበ የሚል ነው ፡፡ ኣት: - “ከመላው ይሁዳና ብንያም ሕዝብን ሰበሰበ” ( ግነትን እና አጠቃላይን ፡ይመልከቱ)

እነርሱ ከእስራኤል የመጡ ናቸው

“ከኤፍሬምና ፣ ከምናሴ እና ከስምዖንም ከእስራኤል የመጡ ናቸው”