am_tn/2ch/13/16.md

3.5 KiB

ከይሁዳ ፊት ሸሹ

እዚህ ላይ “ይሁዳ” የሚለው ቃል የይሁዳን ሰራዊት ይወክላል ፡፡ ኣት: - “በይሁዳ ሰራዊት ፊት ሸሹ” ( የባህሪ ስምን፡ይመልከቱ )

እግዚአብሔር በይሁዳ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው

እዚህ “እጅ” የሚለው ቃል ኃይልን ይወክላል ፡፡ እግዚአብሔር የይሁዳን ሠራዊት የእስራኤልን ሠራዊት ድል እንዲያደርግ ስለማስቻሉ ሲነገር እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት በይሁዳ ሰራዊት እጅ እንዳስገባ ተደርጎ ተገልጻል ፡፡ ኣት: “እግዚአብሔር ይሁዳ እስራኤልን እንዲያሸንፍ አስችሏል” ( የባህሪ ስምን እና ዘይቤያዊን፡ይመልከቱ)

በታላቅ ዕርድ ገደላቸው

ይህ ፈሊጥ ሙሉ በሙሉ ድል አድርጓቸዋል ወይም ብዙ ወታደሮችን ገድለዋል ማለት ነው ፡፡ ኣአት: - “ሙሉ በሙሉ አሸነፋቸው” ወይም “ብዙ ወታደሮቻቸውን አረዱ” ( ፈሊጥን፡ይመልከቱ)

500,000 የተመረጡ ወንዶች

“አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ ወንዶች” ፡፡ “የተመረጡ ሰዎች” የሚለው አገባብ በጦርነት ውስጥ የተካኑትን ከፍ ያሉ ወታደሮችን ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “500,000 ምርጥ ምርጥ ወታደሮች” ( ቁጥሮችን እና ፈሊጥን፡ይመልከቱ)

የእስራኤል ሕዝብ ተገዙ

ይህ በገቢራዊ አረፍተነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ አት: - “የይሁዳ ሠራዊት የእስራኤልን ልጆች አሸነፈ” ( ገቢራዊን እና ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ)

አብያ አሳደደው

“አብያ አሳደደው”

ይሻና… ዔፍሮን

እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርም መታው እርሱም ሞተ

እግዚአብሔር ኢዮርብዓም እንዲሞት ስለማድረጉ ሲጻፍ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምን እንደ መታው ተደርጎ ተጽፏል። ይህ የሚያመለክተው ኢዮርብዓምን እንዲታመም አድርጎት ሊሆን ይችላል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር ኢዮርብዓም እንዲሞት አደረገው” ወይም “እግዚአብሔር ኢዮርብዓም እንዲታመም አደረገው እርሱም ሞተ” ( ዘይቤያዊን እና የሚጠበቅ መረጃን እና ስላልተገለጸ መረጃ ፡ይመልከቱ )

ለእርሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ

“ሚስቶችን . . . ወሰደ” የሚለው አባባል አገባ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኣት: - “አሥራ አራት ሴቶችን አገባ” (ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

አሥራ አራት ሚስቶች… ሀያ ሁለት ወንዶችና አሥራ ስድስት ሴት ልጆች

“14 ሚስቶች… 22 ወንዶች እና 16 ሴት ልጆች” (ቁጥሮቸን ፡ይመልከቱ)

ባህሪው እና ቃላቱ

“በህሪው ፣ እና ንግግሩ” ወይም “ባህሪያቱ ፣ እና የተናገራቸው ነገሮች”

በነቢዩ አዶ ታሪክ ተጽፈዋል

ይህ በገቢራዊ አረፍተነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ነቢዩ አዶ በጻፈለት ታሪክ ውስጥ ይገኛሉ” ( ገቢራዊ ወይም ተብሮአዊ)