am_tn/2ch/12/13.md

3.7 KiB

የአርባ አንድ አመት… አሥራ ሰባት ዓመት

“41 አመቱ… 17 ዓመት” ( ቁጥሮችን ፡ ይመልከቱ)

ስሙን በዚያ ያኖርባት ዘንድ

“ስሙን ማኖር” ለሚለው ሐረግ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “መቀመጥ” የሚገልጽ ነው ፡፡ “ኣት” “እዚያ እንዲቀመጥ” ወይም 2) ባለቤትነትን የሚያመለክት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ኣት: - “የእርሱ እንድትሆን” ( የባህሪ ስምን እና ፈሊጥን ፡ይመልከቱ)

ናዕማ

የሴት ስም ነው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም ፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን አላዘጋጀም

እዚህ “ልብ” የሚለው ቃል ሀሳብን እና ፍላጎትን ይወክላል ፡፡ “ልብን ማንሳት” የሚለው ፈሊጥ አንድ ነገር ለማድረግ መወሰንን ያመለክታል ነው ፡፡ አት: - “ያህዌን ለመፈለግ አልወሰነም” ( የባህሪ ስምን እና ፈሊጥን፡ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ለመፈለግ

እግዚአብሔርን ማምለክ እግዚአብሔርን መፈለግ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጸአል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔርን ማምለክ” ( ዘይቤያዊን፡ይመልከቱ)

የመጀመሪያው እና የመጨረሻው

“ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው።” እነዚህ ሁለት ቃላት አንድ አይነት ትርጉም ሲኖራቸው ሮብዓም ከመንግሥቱ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማብቂያው ድረስ ያከናወናቸውን ነገሮች ያመለክታሉ ፡፡ ኣት: - “ያደረገውን ሁሉ” (ሜሪዝምን ፡ይመልከቱ)

የኢዮርብዓም... የተጻፈ አይደለም?

ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ እና መልሱ አውንታዊ መሆኑን መገመት ይቻላል። መጠይቁ አወያይ መጠይቅ ሲሆን አፅንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል። እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ኣት: - “እነርሱ ተጽፈዋል . . . ኢዮርብዓም” ወይም “ስለእነርሱ ማንበብ ትችላላችሁ… ኢዮርብዓም” ፡፡ ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን እና አወያይ መጠይቅን፡ይመልከቱ)

ሸማያ… አዶ… አብያ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም፡ይመልከቱ)

በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የነበረ የማያቋርጥ ጦርነት

የነገሥታቱ ስም የመሩትን ሠራዊት ይወክላል ፡፡ ኣት: - “የሮብዓም ሰራዊት እና የኢዮርብዓም ሰራዊት በቋሚነት ይሳተፉበት የነበረ ጦርነቶች” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከል ፡ይመልከቱ)

ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ

የሮብዓም ሞቱ መተኛት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። ኣት: - “ሮብዓም ሞተ” ( ዘይቤያዊን እና ዘወርዋራን ፡ይመልከቱ)

በዳዊት ከተማ ተቀበረ

ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “በዳዊት ከተማ ሰዎች ቀበሩት” ( ገቢራዊን ወይም ተቢሮአዊን ፡ይመልከቱ)

በእርሱ ቦታ ነገሠ

“በእርሱ ቦታ” የሚለው ዘይቤ ትርጉሙ“በእርሱ ፋንታ” ነው፡፡ “በሮብዓም ፋንታ ነገሠ” ( ገቢራዊን፡ይመልከቱ)