am_tn/2ch/12/02.md

2.2 KiB

ሆነ

ይህ ሐረግ እርምጃው የት እንደጀመረ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሎአል ፡፡ ቋንቋህ ይህንን የሚገልጽበት መንገድ ካለው እዚህ መጠቀም ትችላለህ ፡፡

በንጉሥ ሮብዓም በአምስተኛው ዓመት

ይህ የሮብዓም የነገሠበትን አራተኛውን ዓመት ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “ሮብዓም በነገሠ በአራተኛው ዓመት” ወይም “በንጉሥ ሮብዓም የአገዘዝ ዘመን” (ተመልከት/ች: የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸን መረጃ እና ሕገኛ ቁጥርን: ይመልከቱ )

የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ

“የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ” እዚህ ላይ ሺሻቅን ከግብፅ ሠራዊት ጋር የሚያመለክት ነው ፡፡ “የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ሺሻቅ

ይህ የወንድ ስም ነው ፡፡ (የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)

ወጣ

ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ጦሩን አዘመተ ወይንም ጥቃት ፈጸመ ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “ለማጥቃት መጣ” (ፈሊጥን: ይመልከቱ)

አንድ ሺ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ስድሳ ሺህ ፈረሰኞች

“1,200 ሠረገሎችና 60,000 ፈረሰኞች” (ቁጥሮችን: ይመልከቱ)

ቁጥር ያልነበራቸው ወታደሮች

ይህ ግነት አንድ ሰው በቀላሉ ሊቆጥረው ከሚችለው በላይ ወታደሮች ነበሩ ማለት ነው። አት: - “ብዙ ወታደሮች” (ግነትን እና አጠቃላይን: ይመልከቱ)

ሊቢያዎች ፣ ሱካዊያን እና ኩሾች

እነዚህ ከሊቢያ ፣ ከሱክ እና ከኢትዮጵያ የመጡ ናቸው ፡፡ የሱካዊያን ቦታ በእርግጠኝነት አይታወቅም ፣ ግን በ ሊቢያ ውስጥ አንድ ክልል ሊሆን ይችላል ፡፡ ( የስሞች አተረጓጎምን እና የማይታወቁትን መተርጎምን ፡ይመልከቱ )