am_tn/2ch/10/16.md

3.9 KiB

እስራኤል ሁሉ

እዚህ “እስራኤል” ለእስራኤል ሰዎች የተሰጠ ስም ነው ፡፡ “ሁሉም” የሚለው ቃል አጠቃላይ ነው ፡፡ ኣት: - “የእስራኤል ሰዎች” (የባህሪ ስምን እና ግነትን እና አጠቃላይን: ይመልከቱ)

ንጉሡ አልሰማቸውም

እዚህ ላይ “ሰዎችን ማድመጥ” የሚለው ለሚናገሩት ነገር ወይም በትክክል የጠየቁትን ስለማድረግ አይደለም ፡፡ ኣት: - “ንጉሡ ህዝቡ እንዲያደርግለት የጠየቀውን አላደረገም ” ወይም “ስለዚህ ንጉሡ ሕዝቡን ችላ አለ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

በዳዊት ዘንድ ምን ድርሻ አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም

የዳዊት ቤተሰብ ስላልሆኑ ፣ የዳዊት የልጅ ልጅ የሆነውን ሮብዓምን ድጋፍ የማድረግ ግዴታ እንደሌለባቸው ለመጦቆም ህዝቡ ይህንን ጥያቄና መግለጫ ይጠቀማሉ ፡፡ ኣት: - “በዳዊት ዘንድ ምንም ድርሻ የለንም። እኛ አናደርግም ከእሴይ ልጅ ዘር ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡ (አወያይ መጠይቅን እና የሚጠበቅ እውቀትን እና የልተገለጸ መረጃን: ይመልከቱ)

በዳዊት ዘንድ ምን ድርሻ አለን?

በአንድ ሰው ውስጥ መካፈል የእርሱ ዘር መሆን እና ዘሮች የሚያገኙትን መልካም ነገሮች መካፈልን ይወክላል። አት: - “እኛ የዳዊት ቤተሰብ አይደለንም” ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም

“የእሴይ ልጅ” የሚለው የእሴይ ልጅ የሆነውን ዳዊት የሚያመለክት ነው። ከአንድ ሰው ውርስ መውረስ የእሱ ዘር መሆን እና ዘሮቹ የሚቀበሉትን መልካም ነገሮች መቀበልን ይወክላል። አት. “ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት አናገኝም” ወይም “ከልጆቹ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አይኖረንም” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

እያንዳንዳችሁ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ

እዚህ “ድንኳን” የሰዎችን ቤት የሚወክል ቃል ነው። ኣት: - “የእስራኤል ሰዎች ሆይ ፣ ወደ ቤታችሁ ሂዱ” ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ዳዊት ሆይ ፣ አሁን ቤትህን ተመልከት

እዚህ “ማየት” የሚለው አንድ ነገርን ለመንከባከብ ፈሊጣዊ ትርጉም ሲሆን “ቤት” ለዳዊት የሥልጣን እና የክብር ዙፋን ምሳሌ ነው ፡፡ ኣት: - “የዳዊት ዘር የሆንከው የራስህን መንግሥት ጠብቅ” (ፈሊጥ እና የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

አዶራም

አዶራም የወንድ ስም ነው። በዚህ ዓረፍተ-ነገር በዕብራይስጡ ጽሑፍ ስሙ አዶራም ተብሎ ተጽፏል ፡፡ (የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)

የገባሮች አለቃ ነበረ

በሰዎች ላይ የበላይ መሆን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የመናገርን ስልጣን ይወክላል። አት: - “በግዳጅ ሠራተኞቹ ላይ ኃላፊ የነበረው” (ዘይቤያዊ : ይመልከቱ)

በድንጋይ ወግረው ገደሉት

አዶራምን በወግር ገደሉት ”

በዳዊት ቤት ላይ ሸፈተ

እዚህ “የዳዊት ቤት” የዳዊት ዘር የሆኑትን ነገሥታት ይወክላል ፡፡ አት: - “ከዳዊት ዘር በሆኑ ነገሥታት ላይ ሸፈጸ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

እስከ ዛሬ

የሚወረስ ሁኔታን ያመለክታል