am_tn/2ch/10/03.md

1.6 KiB

ልከውም ጠሩት

“የእስራኤል ሰዎች ኢዮርብዓምን አስጠሩት”

ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ መጡ

“ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ወደ ሮብዓም መጡ”

እስራኤል ሁሉ መጡ

እዚህ “እስራኤል” ለእስራኤል ሰዎች የተሰጠ ስም ነው ፡፡ “ሁሉም” የሚለው ጠቅለል ያለ ገለጻ ነው ፡፡ አት: “የእስራኤል ሰዎች መጡ”(የባህሪ ስም እና ግነት እና አጠቃላይ : ይመልከቱ)

ቀንበር አክብዶብን ነበር

ከባድ ቀንበር ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን በጣም ከባድ የጉልበት ሥራ እና የጭካኔ አያያዝን ያመለክታል፡፡ አት: - “ጭካኔ አሳየን” ወይም “በጣም ጠንከር ያለ ሥራ እንድንሠራ አስገደደን” ( ዘይቤያዊን : ይመልከቱ)

የአባትህን ከባድ ሥራ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልለን

እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ዓይነት መልዕክት አላቸው፡፡ የቀንበሩ ዘይቤ ሰሎሞን በጭካኔ እንዳደከማቸው ያሳያል ፡፡ ኣት: - “አባትህ የሰጠንን ከባድ ሥራ ቀላል አድርግልን ፤ እርሱ እንዳደረገው ጭካኔ አታሳየን” ( ተመሳሳይነት እና ዘይቤያዊ : ይመልከቱ )

ከሶስት ቀናት በኋላ

“ከ 3 ቀናት በኋላ” (ቁጥሮች: ይመልከቱ)