am_tn/2ch/09/10.md

1.9 KiB

ኪራም

ኪራም የጢሮስ ንጉሥ ነበር። በ 2 ኛ ዜና ምዕራፍ 2 ቁጥር 11 ውስጥ ስሙን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ ኣት: - “የጢሮስ ንጉሥ ኪራም” ወይም “ንጉሥ ኪራም” ( የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)

ኦፊር

ይህ የቦታ ስም ነው ፡፡ የሚገኝበት ቦታ አይታወቅም ፡፡ በ 2 ኛ ዜና ምዕራፍ 8፡ 18 ውስጥ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም : ይመልከቱ)

የሰንደል እንጨት

የሰንደል እንጨት በሊባኖስ ውስጥ የሚያድግ የዛፍ አይነት ነው። ንጉሥ ኪራም እንዲህ ዓይነቱን እንጨት ለሰሎሞን ላከ። በ 2 ኛ ዜና 2 8 ውስጥ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡

ንጉሡም ደርብ ሠራ . . . በገናንና መሰንቆዎችን ሠራ

ንጉሱ ሰራተኞቹን እነዚህን እቃዎች እንዲሠሩ ማድረጉን ደራሲው ሲጽፍ ንጉሡ እራሱ እንደሠራው አድርጎ ጽፏል፡፡ አት: - “ንጉሡ ሠራተኞቹን ደረጃዎችን …. በገናዎችን ፣ መሰንቆዎችን እንዲሠሩ አደረገ ፣” ወይም የንጉሡ ሠራተኞች ደረጃዎችን … ደግሞም በገናዎችን እና መሰንቆዎችን ሠሩ፡፡ ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ከዚህ በፊት በይሁዳ ምድር እንደዚህ ያለ እንጨት ታይቶ አይታወቅም ነበር

ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ አት: - “ከዚህ በፊት በይሁዳ ምድር እንደዚህ ያለ እንጨት ማንም አይቶ አያውቅም” ( ገቢራዊን እና ተብሮአዊን: ይመልከቱ)