am_tn/2ch/08/01.md

1.8 KiB

ይህ ተከሰተ

እዚህ ይህ ሐረግ የታሪኩን አዲስ ክፍል መጀመሪያ ለመጠቆም የሚያገለግል ነው፡፡ ቋንቋህ ይህንን የሚያሳይበት መንገድ ካለ እዚህ ቦታ ላይ መጠቀም ትችላለህ ፡፡

ሃያ ዓመት በተጸፈጸመ ጊዜ

“ከ 20 ዓመት በኋላ” (ቁጥሮችን: ይመልከቱ)

ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት ሠራ

ስለ ሰሎሞን ቤተመቅደሱ እና ቤተ መንግሥቱ እንዲሠሩ ለህዝቡ ትእዛዝ ማስተላለፍ እና እንዴተ መሠራት እንዳለበት መግለጽ ደራሲው ሲጽፍ ሰሎሞን ራሱ እንደሠራው አስመስሎ ጽፏል ፡፡ AT(አማራጭ ትርጉም): - “ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት አሠራ” ወይም “በሰሎሞን መሪነት ቤተ መቅደሱና ቤተመንግስቱ ተሠራ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ኪራም

ኪራም የጢሮስ ንጉሥ ነበር። በ 2 ኛ ዜና ምዕራፍ 2 ቁጥር 11 ውስጥ ስሙን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ አት: - “የጢሮስ ንጉሥ ኪራም” ወይም “ንጉሥ ኪራም” (የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)

ሰሎሞም ኪራም የሰጠውን ከተሞች ሠራ

ሰለሞን ሌሎች ሰዎች እንደገና እንዲገነቡ ስለማዘዙ ደራሲው ሲጽፍ እሱ ራሱ እንደገነባው በማስመሰል ጽፏል ፡፡ AT: -“ሰለሞን ኪራም ለእርሱ የሰጡት ከተሞች እንዲገነቡ አደረገ” ወይም “ሰሎሞን አዘዘ ህዝቡም ኪራም የሰጣቸውን ከተሞች ገነቡ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)