am_tn/2ch/07/16.md

2.6 KiB

ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ነው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የእግዚአብሔር ስም ራሱን ይወክላል ፡፡ ኣት: - “ለዘላለም በዚያ እሆን ዘንድ” ወይም 2) የእግዚአብሔር ስም የእርሱን ማንነት ይወክላል ፣ እና ስሙ በዚያ መኖሩ ሰዎች እርሱን በዚያ እያመለኩ አንዳለ ያመለክታል ። ኣት: - “ሰዎች ለዘላለም በዚያ ያመልኩኝ ዘንድ ” ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ዘወትር ዓይኖቼና ልቤ በዚያ ይኖራሉ

እዚህ “ዐይኖቼ” የሚለው የእግዚአብሔርን ጥንቃቄ ያመለክታል ፣ “ልቤ” የሚለው ደግሞ ፍቅሩን ያመለክታል ፡፡ እነዚህ በቤተ መቅደሱ መገኘታቸው እርሱ ቤተ መቅደሱን እንደሚጠብቀው ያመለክታሉ ፡፡ አት: - “ለዘላለም እንከባከበዋለሁ ደግሞም እጠብቀዋለሁ” ( የባህሪ ስምን እና የሚጠበቅ እውቀትን እና የልተገለጸ መረጃን: ይመልከቱ )

ለአንተም

እዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ንጉስ ሰሎሞንን ያመለክታል።

አንተም አባትህ ዳዊት እንደ ሄደ በፊቴ ብትሄድ

እዚህ መሄድ ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን መኖር የሚል ትርጉም አለው። በእግዚአብሔር ፊት መሄድ እሱን በመታዘዝ መኖርን ይወክላል ፡፡ አት: - “እንደ አባትህ እንደ ዳዊት ብትታዘዘኝ ”( ተመልከት/ች: ዘይቤያዊ)

አባትህ ዳዊት

ሰሎሞን ከዳዊት ልጆች አንዱ ነበር ፡፡

ሥርዓቴንና ፍርዴንም ብትጠብቁ

“ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን መታዘዝ”

የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ

እዚህ ዙፋኑ መግዛትን ያመለከታል ፡፡ የሰሎሞንን መንግሥት ዙፋን ማጽናት ማለት ሰሎሞን በእስራኤል የሚገዘ ዘር እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “የአንተ ዘሮች በመንግሥትህ ላይ እንዲገዙ አደርጋለሁ” ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ዘሮችህ በእስራኤል ውስጥ ገዥ መሆናቸው መቼም ቢሆን አይወድቅም

ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለጽ ይችላል ፡፡ አት: - “ከዘርህ መካከል አንዱ ሁል ጊዜ በእስራኤል ገዢ ይሆናል” ወይም “ዘርህ በእስራኤል ውስጥ ሁል ጊዜ ይገዛሉ”