am_tn/2ch/07/13.md

3.4 KiB

ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን ብዘጋ

እዚህ “ሰማያት” ሰማይን የሚያመለክት ሲሆን እግዚአብሔር ዝናብን የሚያከማችበት ጋን ተደርጎ ተገልጾአል ፡፡ በ 2 ዜና 6፡ 26 ላይ የሚገኘውን ተመሳሳይ ሐረግ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት ፡፡ አት: - “ዝናብ ከሰማያት እንዲዘንብ ካልፈቀድኩኝ” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

ምድሪቱን ቢበላ

“ምድር ” የሚለው ቃል በምድር ላይ ያሉትን እፀዋትን እና ሰብሎችን ይወክላል ፡፡ ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

በሕዝቤ ላይ በሽታን ብልክ

“በሽታ መላክ” የሚለው በሽታ እንዲከሰት ማድረግን ያመለክታል ፡፡ አት: - “ሕዝቤን በበሽታ እንዲይዙ ባደርግ” (ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

በስሜ የተጠሩ ህዝቤት

እዚህ በእግዚአብሔር ስም መጠራት የሚለው ፈሊጥ ሲሆን የእግዚአብሔር ንብረት መሆን ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “የእኔ የሆነ” ( ፈሊጥን : ይመልከቱ)

ፊቴን ፈልጉ

እዚህ የእግዚአብሄር ፊት እነርሱን መቀበሉን ያሳያል ፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች “ፊቴን ፈልጉ” የሚለው የሚያመለክተው 1) ወዲውኑ እርሱን ይቅርታ መጠየቅ። አት: - “እነርሱን ይቅር እንድል ለምኑኝ” ወይም 2) እርሱን ለማስደሰት አጥብቆ መፈለግ ፡፡ አት: - “እኔን ለማስደሰት ምረጥ” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ

እዚህ “ቢመለሱ”የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን አንድን ነገር ከመሥራት መቆጠብ ማለት ነው ፣ “መንገዶች” የሚለው ደግሞ ባህሪን ያመለክታሉ ፡፡ አት: - “ክፉ ባሕርያቸውን አቆሙ” ወይም “መጥፎ ነገሮችን ማድረጋችሁን አቁሙ” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

ምድራቸውን ይፈውሳል

ብዙ የማይበቅለው መሬት የታመመ ነው ይባላል። አት: - “ምድራቸውን መልሶ መልካም ያድርገዋል” ወይም “ምድራቸው ጥሩ ሰብል እንዲያበቅል ያደርጋል” (ተስብኦትን: ይመልከቱ)

ዓይኖቼ ይከፈታሉ

የተከፈቱ አይኖች ዘይቤ ሲሆን ማየትን ማለት ነው ፡፡ እዚህ በትኩረት መመልከትን ይወክላል። አት: - “ወደ እናንተ በትኩረት አመለከታለሁ” ወይም “እመለከታችኋለሁ”( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ለጸሎት ጆሮቼ ያደምጣሉ

ጆሮቼ ያደምጣሉ የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን በትኩረት ማዳመጥ ማለት ነው ። ኣት: - “ጸሎቶችን እሰማለሁ” (የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

በዚህ ቦታ ለሚጸለይ ጸሎት

ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል። ኣት: - “በዚህ ቦታ ለምትጸልዩት ጸሎት” ወይም “ለእናንተ በዚህ ቦታ ወደ እኔ ስትጸልዩ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን: ይመልከቱ)