am_tn/2ch/07/08.md

2.6 KiB

ከእርሱ ጋር እስራኤልን ሁሉ

ይህ አጠቃላይ ቃል የሚያመለክተው በኢየሩሳሌም በዓል ላይ የነበሩትን ነው ነውንጂ በእስራኤል ለሚኖሩ ሁሉ አይደለም ፡፡ (ተመልከት/ች: ግነት እና አጠቃላይ)

ከሌባ ሐማት እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ

ሌባ ሃማት ከእስራኤል በስተ ሰሜን ሲሆን፥ የግብፅም ወንዝ ከእስራኤል በስተ ደቡብ ነበር። እነዚህ ከሁሉም የእስራኤል ክፍሎች ሰዎች በበዓሉ ላይ እንደነበሩ ለማሳየት ያገለግላሉ ፡፡ አት: - “ከሰሜን ከሐማት ጀምሮ እስከ ደቡብ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ” ( የሚጠበቅ እውቀት እና የልተገለጸ መረጃን እና ሜሪዝምን እና የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)

ስምንተኛው ቀን

“ስምንተኛው” የሚለው ቃል “8” የሚል መደበኛ ቁጥርን ያመለክታል ፡፡ ( ሕገኛ ቁጥርን: ይመልከቱ)

እጅግ ታላቅ ጉባኤ

ይህ ልዩ ኃይማኖታዊ ስብሰባ ነበር ፡፡

መሠዊያውን ቀደሱ

እዚህ “መቀደሱን ጠበቁ” የሚለው አገላለጽ “መቀደሱን ማክበር” ማለት ነው ፡፡( ፈሊጥን: ይመልከቱ)

በሰባተኛው ወር በሀያ ሦስተኛው ቀን

ይህ በዕብራይስጥ የቀን አቆጣጠር ሰባተኛ ወር ነው። ሀያ ሦስተኛው ቀን በምዕራባዊው የቀን አቆጣጠር የጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ነው። ( የዕብራዊያንን ወራትን እና ሕገኛ ቁጥርን : ይመልከቱ)

በደስታ እና በሐሴት በተሞሉ ልቦች

“ደስታ” እና “ሐሴት” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው ፡፡ በአድነት የደስታውን ትልቅነት ያጎላሉ ፡፡ አት: - “በጣም በተደሰቱ ልቦች” ወይም “እጅግም ደስ አላቸው” ( ድግግሞሽን: ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ስላሳያቸው ቸርነት

“እግዚአብሔር ድንቅ ቸርነቱን ስላሳየ” ወይም “ እግዚአብሔር በጣም መልካም ስለ ሆነ”

ህዝቡ እስራኤል

“የእግዚአብሔር ህዝብ እስራኤል፡፡” “የእርሱ ህዝብ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር ለእስራኤል ታማኝ መሆኑን ያጎላል፡፡ (መለየትን ከማስታወቅ እና ከማስታዎስ ጋር : ይመልከቱ)