am_tn/2ch/06/36.md

7.9 KiB

አያያዥ መግለጫ

ንጉሥ ሰሎሞን ጸሎቱን ቀጠለ ፡፡

ቢበድሉ … አንተ ብትቆጣ…እነርሱም ቢገነዘቡ … ንስሐ ቢገቡ… ቢሉ …ቢመለሱ… ቢለምኑህ

ሰለሞን በሚናገርበት ጊዜ እነዚህ ግምታዊ ሁኔታዎች አልተከሰቱም ፣ ነገር ግን ሰለሞን ወደፊት እንደሚከሰቱ ያውቅ ነበር ፡፡ ያልተከናወኑ ግን ወደፊት ሊከሰቱ ስለሚችሉ ክስተቶችን የሚገልጹ አገላለጾችን በቋንቋህ ካሉ ተጠቀም። (መላምታዊ ሁኔታዎችን : ይመልከቱ)

ለጠላት አሳልፈህ ስጣቸው

እዚህ ላይ “ለጠላት አሳልፈው ስጣቸው” ጠላት እነሱን እንዲይዛቸው መፍቀድን ያመለክታል ፡፡ ( ዘይቤያዊን : ይመልከቱ)

ጠላት ማርኮ ቢወስዳቸው

እዚህ “ይማርኳቸዋል” አገራቸውን ለቀው እንዲሄድ ማስገደድን ያመለክታል ፡፡ አት: - “ጠላቶቻቸው እንዲሄዱ ያስገድዷቸዋል” (ዘይቤያዊን : ይመልከቱ)

በተማረኩበትም አገር ሆነው

ይህ ገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ጠላቶቻቸው በምርኮ የወሰዷቸው አገር” (ገቢራዊ ወይም ተብሮአዊ : ይመልከቱ

በፊትህ ሞገስን ለማግኘት ቢፈልጉ

“ምሕረት እንድታደርግላቸው ቢለምኑህ”

በድለናል ኃጢአትም ሠርተናል ፡፡ ክፉም አድርገናል

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች አንድ ዓይነት ሲሆኑ የሰዎቹ አካሄድ ምን ያህል መጥፎ እንደነበረ አጉልተው ያሳያሉ። (ተመሳሳይነቶችን : ይመልከቱ)

በድለናል ኃጢአትም ሠርተናል

ቃላቶቹ በመሠረቱ አንድ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሕዝቡ ምን ያህል ኃጢአት እንደሠሩ አጉልቶ ያሳያል ፡፡ (ድግግሞሽን: ይመልከቱ)

እነርሱ ወደእናንተ ቢመለሱ

እዚህ “ወደአንተ ቢመለሱ” ለያህዌህ እንደገና መገዛትን ያመለክታል ፡፡ አት: - “እንደገና ይገዙለታል” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

በፍጹም ልባቸው እና በፍጹም ነፍሳቸው

“በሙሉ ልባቸው” እና “በሙሉ ነፍሳቸው” የሚሉት ሐረጎች ፈሊጣዊ አገላለጽ ሲሆኑ “ሙሉ በሙሉ” እና “በሁለንተናቸው” የሚል ትርጉም አላቸው ፡፡ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ፡፡ አት: “ሙሉ በሙሉ” ( ፈሊጥን እና ድግግሞሽን: ይመልከቱ )

ምርኮኛ አድርገው በወሰዷቸው አገር

“ጠላቶቻቸው ምርኮኛ አድርገው በወሰዷቸው አገር”

ወደ አገራቸው ብጸሊዩ

ይህ እስራኤልን ያመለክታል ፡፡ ወደ እስራኤል መጸለያቸው ወደእስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንደጸለዩ ያሳያል ፡፡ አት: - “ወደ አገራቸው አቅጣጫ እየተመለከቱ መጸለይ” (ምሳሌያዊ ድርጊትን: ይመልከቱ)

ወደመረጥኸው ከተማ

ይህ ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ነው።

እኔ የሠራሁት ቤት ነው

ሰሎሞን ፣ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ ስለማዘዙ እና እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ስለመናገሩ ሲገልጽ እሱ ራሱ እንደሠራው አስመስሎ ተናግሯል ፡፡ አት: - “ሕዝብህ በእኔ መሪነት የሠራው ይህ ቤት” ወይም “እኔና ሕዝብህ የሠራነው ይህ ቤት” (ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን: ይመልከቱ)

ለስምህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የያህዌህ ስም ራሱን ይወክላል ፡፡ አት: - “ለአንተ” ወይም 2) የያህዌህ ስም ማንነቱን ይወክላል። አት: - “ስለስምህ”(የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

ወደ ጸሎታቸው እና ልመናቸው

“ጸሎት” እና “ልመና” የሚሉት የነገሮች ስሞች እንደ ግሶች ሊገለጹ ይችላሉ። አት: - “ወደ አንተ ሲጸልዩ ወደ ልመናቸው” (ድግግሞሽን : ይመልከቱ)

አሁን

እዚህ “አሁን” የሚለው ቃል ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ነጥብ ትኩረትን ለመሳብ ይጠቅማል ፡፡

ዓይኖችህ ይከፈቱ

የተከፈቱ አይኖች ልማዳዊ አነጋገር ሲሆን ማየት ማለት ነው ፡፡ እዚህ በትኩረት መመልከትን ያመለክታል። ኣት: - “እባክህን ወደኛ አትኩር ” ወይም “እባክህን እኛን ተመልከት” ( የባህሪ ስምን : ይመልከቱ )

ጆሮችህ ጸሎትን የሚያደምጡ ይሁኑ

የሚያዳምጡ ጆሮዎች በትኩረት ማዳመጥን የሚወክል ነው፡፡። ኣት: - “እባክህ ጸሎትን አድምጥ” ( የባህሪ ስምን : ይመልከቱ)

በዚህ ሥፍራ ወደሚሆነው ጸሎት

ይህ በገቢራዊ ቅርጽ ሊገለፅ ይችላል። ኣት: - “በዚህ ቦታ ለምናቀርበው ጸሎት” ወይም “በዚህ ቦታ ጸሎት ስናቀርብ ወደኛ ተመልከት” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን : ይመልከቱ)

አቤቱ አምላክ ሆይ ፣ ወደ ማረፊያ ቦታህ ተነሣ

ይህ እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠ ይመስል ከዙፋኑ እንዲነሳና ወደዚህ ቦታ እንዲመጣ ይጠይቃል ፡፡ አት: - “አቤቱ አምላክ ሆይ ፣ ተነስና ወደ ማረፊያህ ስፍራ ተመለስ” ( ዘይቤአዊን : ይመልከቱ)

የኃይልህ ታቦት

“የኃይልህ ተምሳሌት የሆነች ታቦት”

ካህናቶችህ… መዳንን ይልበሱ ፤

“መዳን” የሚለው የነገሮች ስም “ማዳን” በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1 ኛ) መዳንን መልበስ ማለት ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን መዳንን ማግኘት ማለት ነው ፡፡ ኣት: “ካህናቶችህ… እንዳዳንካቸው … ያውቁ” ወይም 2) መዳንን መልበስ ማለት ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን መዳንን ማሳየት ማለት ነው ፡፡ አት: - “ካህናቶችህ… ሰዎችን እንዴት እንደምታድኑ ያሳዩ” (ተመልከት/ች: ዘይቤያዊን እና የረቂቅ ስሞችን : ይመልከቱ)

የቀባኸውን ሰው ፊት ከአንተ አትመልስ

የአንድን ሰው ፊት ማዞር እርሱን አለመቀበልን ያሳያል ፡፡ አት: - “የቀባሀውን አትጣል” (ተመልከት/ች: ዘይቤያዊ) የቀባኸው የተቀባህ ሰው ”ቅቡዕነት በእግዚአብሔር የመመረጥ መግለጫ ነው። ንጉሥ ሰሎሞን ምናልባት ስለ ራሱ እየተናገረ ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ አት: - “የቀባኸው” ወይም “ንጉሥ እሆን ዘንድ የመረጥኸኝ እኔ” (የባህሪ ስም እና ገቢራዊ ወይም ተብሮአዊ: ይመልከቱ)

ለአገልጋይህ ለዳዊት ያደረከውን የቃል ኪዳን ታማኝነትህን አስብ

“ሥራህ” የሚለው ሐረግ “ያደረግከው” በሚል ሐረግ ሊገለጽ ይችላል ፡፡ “ኣት” “ለባሪያህ ለዳዊት ስለ ቃል ኪዳንህ ታማኝነት ስትል ያደረከውን አስታውስ ”

በልብህ ጠብቅ/አስብ

“አስታውስ”