am_tn/2ch/06/32.md

2.8 KiB

አያያዥ መግለጫ

ንጉሥ ሰሎሞን ጸሎቱን ቀጠለ ፡፡

ማን-ስለታላቁ ስምህ ብርቱውም እጅህ፣ እና በተዘረጋ ክንድህ - መጣ

እንግዶች የሚመጡት ስለ እግዚአብሔር ታላቅነት ስለሰሙ ነው ፡፡ አት: - “ ስለ ታላቅ ስምህ ፣ ስለ ኃያል እጅህና ስለ ተዘረጋ ክንድህ የሚሰማ- ከመጣ” ( የሚጠበቅ እውቀት ወይም ያልተገለጸ መረጃ : ይመልከቱ)

ታላቅ ስምህ

እዚህ የእግዚአብሔር ስም ማንነቱን ያሳያል ፡፡ አት: - “ታላቅ ስምህ” ወይም “ታላቅነትህ”((ተመልከት/ች: ዘይቤያዊ)) ኃያል እጅህንና የተዘረጋ ክንድህ እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ ተመሣሳይ ትርጉም ያላቸውና የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክቱ ናቸው ፡፡ ((ተመልከት/ች: ድግግሞሽ እና የባህሪ ስም ))

ወደዚህ ቤት ጸለየ

አንድ ሰው ወደ ቤተ መቅደስ ሲጸልይ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ እንዳለ ያሳያል። ((ተመልከት/ች: ምሳሌያዊ ድርጊት))

ስምህን እንዲያውቁ

እዚህ የእግዚአብሔር ስም ማንነቱን ይወክላል ፡፡ አት: - “ስምህን እንዲያውቅ” ወይም “ታላቅነትህን እንዲያውቅ” (የባህሪ ስምን : ይመልከቱ)

እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል /እንዲፈሩህ

“ያንተ ሕዝብህ እስራኤል ስምህን እንደሚያውቅ እና እንዲፈሩህ”

እኔ የሠራሁት ይህ ቤት በስምህ ተጠርቷል

“በስምህ ተጠርቷል” የሚለው ሐረግ የሚያሳየው እግዚአብሔር ቤቱን እንደያዘውና የቤቱ ባለቤት እንደሆነ ነው ፡፡ ይህ በገቢራዊ አረፍተ ነገር ሊገለፅ ይችላል ፡፡ አት: - “እኔ የሠራሁት ይህንን ቤት የራስህ አድርገው” ( ገቢራዊ ወይም ተብሮአዊ : ይመልከቱ)

ይህ የሠራሁት ቤት

ሰሎሞን ፣ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ ስለማዘዙ እና እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ስለመናገሩ ሲገልጽ እሱ ራሱ እንደሠራው አስመስሎ ተናግሯል ፡፡ በ 2 ዜና 6 18 ውስጥ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደቶሮጎምከው ተመልከት ፡፡ አት: - “ሕዝብህ በእኔ መሪነት የሠራው ይህ ቤት” ወይም “እኔና ሕዝብህ የሠራነው ይህ ቤት” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መተካት: ይመልከቱ)