am_tn/2ch/06/16.md

2.4 KiB

አያያዥ መግለጫ

ንጉሥ ሰሎሞን ጸሎቱን ቀጠለ ፡፡

ቃል የገባኸውን ጠብቅ

ይህ ጥያቄ ነው ፡፡ አንድ ሰው የተናገረውን ጠበቀ ማለት ፈሊጣዊ አገላለጽ ሲሆን አንድ ሰው ቃል የገባውን ፈፀመ የሚል ትርጉም አለው ፡፡ አት: - “እባክህን የገባኸውን ቃል አድርግ” (ስለፈሊጥ: ይመልከቱ)

ሰው አታጣም

እግዚአብሔር ዳዊት ሰው እንደሚያገኝ ሲናገር ዳዊትን የሚወርሰው ከዳዊት ዘር እንደሚሆን ይጠቁማል ፡፡ ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለጽ ይችላል ፡፡ አት: - “አንተ ሁል ጊዜ ከዘርህ የሚተካህ ይኖርሃል” (የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸን እና እጥፍ አሉታዊን : ይመልከቱ)

በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው በፊቴ

እዚህ “በፊቴ” የሚለው ቃል/ሐረግ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ሰውየውን እንደሚመርጥ እና ሰውየውም እግዚአብሔርን መታዘዝ እንደሚፈልግ ያሳያል ፡፡ (የሚጠበቅ እውቀትን እና የልተገለጸን መረጃ: ይመልከቱ)

በእስራኤል ዙፋን ላይ ለመቀመጥ

ዙፋኑ የሚያመለክት በዙፋኑ ላይ የሚቀመጠውን ሰው ተግባር ነው ፡፡ አት: - “በእስራኤል ላይ ይገዛል” (የባህሪ ስም : ይመልከቱ)

አንተ በፊቴ እንደ ሄድኸው በሕጌ ይሄዱ ዘንድ

አንድ ሰው የሚያሳየው በህሪይ ግለሰቡ በመንገድ ላይ እንደተጓዘ ተደርጎ ተገል። አት: - “እንደ ታዘዝከኝ ሕጌን እንዲታዘዙ” ወይም “ለእኔ ታማኝ እንደሆንኸ ለሕጌ ታማኝ ይሁኑ” (ዘይቤያዊን : ይመልከቱ)

ለአገልጋይህ ለዳዊት የተናገርኸው ቃል ይጽና

“ለባሪያህ ለዳዊት የነገርኸውን ቃል እንድትፈጽመው እፈልጋለሁ”

ቃልህ ይጽና

ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊተረጎም ይችላል። አት: - “ቃልህን አጽና” ወይም “ቃልህን ፈጽም” (ጥራዝ 2: ትርጉም: ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን: ይመልከቱ)

ቃልህ

“ቃል የገባኸው ነገር”