am_tn/2ch/06/01.md

1.9 KiB

እግዚአብሔር ብሎአል

ሰሎሞን ስእግዚአብሔር ሲናገር ለሌላ ሰው የሚናገር ይመስላል ይህም ለእግዚአብሔር ያለውን አክብሮት ለማሳየት ነው፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር ሆይ ፣ አንተ አልህ” ( አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ መደብ ሰብዓዊን: ይመልከቱ)

በወፍራም ጨለማ ውስጥ

እዚህ “ወፍራም” የሚለው ቃል ጨለማው እጅግ በጣም ከባድ መሆኑን ያሳያል ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ሰዎች እንዲመለከቱት እንደማይፈቅድ ሲናገር በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር አስመስሎ ተናግሯል፡፡ ኣት: - “በታላቅ ጨለማ ውስጥ” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

እጅግ ከፍ ያለ መኖሪያ ቤት ሠራሁልህ

ሰሎሞን ፣ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ ማዘዙን እና እንዴት መሥራት እንዳለባቸው መናገሩን እርሱ ራሱ እንደገነባው አስመስሎ ይናገራል ፡፡ ኣት: - “እኔና ሕዝብህ እጅግ ከፍ ያለ መኖሪያ ሠርተንላችኋል” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ ስለመወከል : ይመልከቱ )

ከፍ ያለ መኖሪያ ሠራሁልህ

በጣም አስፈላጊ ለሆነ ሰው የሚመጥን የሚያምር ቤተ

የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቆመው ነበር

“ማኅበሩ ሁሉ” የሚለው ሐረግ አጠቃላይ ነው ፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ እስራኤልላዊ ቆሞ ነበር ማለት ሳየሆን ፣ እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ቆመው ነበር ማለት ነው ፡፡ ኣት: - “የእስራኤል ሕዝብ በዚያ ቆመው ነበር” ( ግነትን እና አጠቃላይን : ይመልከቱ)