am_tn/2ch/01/14.md

2.2 KiB

1,400 ሠረገሎች

“አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረገሎች” ( ቁጥሮችን: ይመልከቱ)

አሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች

“12,000 ፈረሰኞች” ( ቁጥሮችን: ይመልከቱ)

በሰረገሎች ከተሞች ውስጥ

ይህ ሰረገሎቹን ያከማቹትን ከተሞች የሚያሳይ ነው ፡፡

ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው

ተራኪው በኢየሩሳሌም ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ ብር ለማጉላት የተጋነነ ትረካ ይጠቀማል ፡፡ አት: - “ንጉሡ በኢየሩሳሌም እጅግ ብዙ ብር ነበረው ፣ ብሩ በምድር ላይ እንዳለ ድንጋይ ብዙ ነበር” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከል እና አጠቃላይን: ይመልከቱ)

የሾላ ዛፎች

ይህ በለስ የሚመስል ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው። ( የማይታወቁትን ይተርጉሙ)

ለሰሎሞን ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ ስለማስመጣትን

“ማስመጣት” አንድን ነገር ከሌላ ሀገር ወደ አንድ ነገር የማምጣት ተግባር ነው። ይህ እንደ ግስ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ አት: - “ሰሎሞን ፈረሶቹን ከግብጽና ከቀዌ ያስመጣ ነበር” ( የረቂቅ ስሞችን: ይመልከቱ)

ቀዌ

ይህ የክልል ስም ነው ፡፡ አንዳንዶች ቀዌን በትንሹ እስያ ውስጥ ከሚገኘው ከኪልቅያ ጋር አንድ ነው ብለው ያስባሉ ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ )

በዋጋ

“በተቆረጠለት ዋጋ” ወይም “በገንዘብ”

ስድስት መቶ ሰቅል ብር… 150 ሰቅል

አንድ ሰቅል ከ 11 ግራም ጋር እኩል የሆነ የክብደት መለኪያ ነው። ኣት: - “6.6 ኪሎ ግራም ገደማ ብር… ወደ 1.7 ኪሎ ግራም” ( መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክብደትን: ይመልከቱ)

ስድስት መቶ

“600” ( ቁጥሮችን: ይመልከቱ)

ተልኳል

አንድን ነገር ከአንዱ አገር ወደ ሌላ ሀገር መላክ