am_tn/2ch/01/08.md

2.5 KiB

ለዳዊት ታላቅ ቃል ኪዳናዊ ታማኝነትን አሳይተሃል

“ታማኝነት” የሚለው የረቂቅ ስም “ታማኝነት” ወይም “በታማኝነት” ተብሎ ሊገለፅ ይችላል። ኣት: “ለዳዊት እጅግ ታላቅ ፍቅርን አሳይተኃል” ወይም “ለዳዊት በጣም ታማኝ ነበርኽ” ( የረቂቅ ስሞችን: ይመልከቱ)

አሁን

እዚህ “አሁን” የሚለው ቃል ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ነጥብ ትኩረትን ለመሳብ ይጠቅማል ፡፡

ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም

ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ታደርገው ዘንድ ለአባቴ ለዳዊት ቃል የገባውን እባክህን አድርግ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን: ይመልከቱ)

እንደ ምድር ትቢያ በሆነው በብዙ ህዝብ ላይ

ይህ ምሳሌ የእስራኤላዊያንን ብዛት ያጎላል ፡፡ ኣት: - “ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህዝብ” ወይም “እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ” ( ዘይቤያዊን: ይመልከቱ)

ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ

እነዚህን ያልተለመዱ ረቂቅ ስሞች ለማስወገድ “ጥበብ” እና “ዕውቀት”ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ኣት ““ ጥበበኛ እንድሆን እና ብዙ ነገሮችን እንዳውቅ አድርገኝ ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን: ይመልከቱ)

በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማነው?

እዚህ “ፈራጅ” ማለት ገዥ ማለት ወይም መግዛት ማለት ነው ፡፡ ሰሎሞን ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ብዙ ሰዎችን መግዛት የማይቻል መሆኑን ለመግለጽ ጥያቄን ይጠቀማል ፡፡ ኣት: - “ያለአንተ እርዳታ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ህዝብ ሁሉ ማንም ሊፈርድ ይችላል።” ( አወያይ መጠይቅን: ይመልከቱ)

ምክንያቱም ይህ በልብህ ውስጥ ነበር

እዚህ “ልብ” ምኞትን ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “ይህ የአንተ ፍላጎት ነበር” ወይም “አንተ የፈለከው ይህንን ነውና” ( የባህሪ ስምን: ይመልከቱ)

የሚጠሉህን ሰዎች ሕይወት አይደለም

ወይም “የሚጠሉህን ለማሸነፍ ” ወይም “ጠላቶችህን ለመግደል”