3.0 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡
እንደ ዩ.ዲ.ቢ. በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የተከናወኑትን ክስተቶች ቅደም ተከተል እንደገና ማስተካከል ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ፡፡ (የክስተቶች ቅደም ተከተልን : ይመልከቱ)
ለእስራኤል ሁሉ ፣ ለአለቆች . . .ለአባቶች ቤቶቸ መሪዎቸ ተናገረ፡፡
እዚህ “እስራኤል ሁሉ” ማለት ቀጥሎ የተጠቀሱትን ሰዎች ማለት ነው ፡፡ እነሱ እስራኤልን ሁሉ ይወክላሉ ፡፡ አት: - “ለአለቆች . . . ለአባቶች ቤት አለቆች ተናገረ”
ሻለቆች እና መቶ አለቆች
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እነዚህ ቁጥሮች እነዚህ አለቆች የሚመሩትን ወታደሮች ብዛት ያመለክታሉ ፡፡ አት: - “የ 1000 ወታደሮች አዛዦች እና የ100 ወታደሮች አዛዦች” ወይም 2) “ሺህ” እና “መቶ” ተብለው የተተረጎሙት ቃላት ትክክለኛ ቁጥሮችን አይወክሉም ፣ ግን ትላልቅና ትናንሽ ወታደራዊ ምድቦች ስሞች ናቸው። አት: - “የትላልቅ የጦር ምድቦች አዛዦች እና የትናንሽ የጦር ምድቦች አዛዦች ( ቁጥሮችን ፡ይመልከቱ)
በእስራኤል ላሉ አለቆች(ልኡል) ሁሉ፣ የአባቶቹ ቤቶች መሪዎች
እዚህ ላይ “የአባቶች ቤቶች መሪዎች” የሚለው መሳፍንቱን የበለጠ ይገልፃሉ ፡፡ አት: - “በእስራኤል ሁሉ ላይ ለሚገኙ መሳፍንት ሁሉ ማለትም የአባቶች ቤቶች መሪዎች”
ለሁሉም መስፍን
እዚህ “መስፍን” ማለት በአጠቃላይ መሪዎች ማለት ነው ፡፡ የግድ የንጉሡ ልጆች ላይሆኑ ይቺላሉ፡፡ አት: - “ለመሪ ሁሉ”
የአባቶቹ ቤቶች መሪዎች
እዚህ “ራሶች” በጣም አስፈላጊ የሆነ አካል ምሳሌ ነው ፡፡ “ቤቶች” ቤተሰቦችን ይወክላሉ ፡፡ አት: - “በእስራኤል የእስራኤል ነገዶች መሪዎች ናቸው” ( ዘይቤያዊ እና የባህሪ ስምን : ይመልከቱ)
ከቂርያትይዓሪም
ከኢየሩሳሌም በስተ ምዕራብ 9 ማይል ያህል ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ ( የስሞች አተረጓጎም: ይመልከቱ)
ድንኳን ተከለ
“ድንኳን አዘጋጁ”
በሆርም ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ
ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “የሆርም የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የነሐስ መሠዊያ” ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን: ይመልከቱ)
የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው ፡፡ ( የስሞችን አተረጓጎም: ይመልከቱ)