am_tn/1ti/05/05.md

1.3 KiB

1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡5-6

ይሁን እንጂ እውነተኛዋ በልታቴ ማንም የላትም "ይሁን እንጂ እውነተኛ ባልቴት የሆነች ሴት የሚያግዛት ቤተሰብ የላትም" ሁል ጊዜ በጥያቄ እና በጸሎት በእርሱ ፊት ትቀርባለች "በእግዚአብሔር ፊት ጥያቄዎቿን እና ጸሎቶቿን ይዛ ዘወትር ትቀርባለች" ጥያቄዎቿን እና ጸሎቷን እነዚህ ሁለት ቃላት ትርጉማቸው በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ቃላት ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ ላይ የተጠቀማቸው ባልቴቷ ምን ያህል እንደሚትጸልይ አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-doublet]]) ቀን እና ሌሊት አማራጭ ትርጉም፡ “ሁል ጊዜ”፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-merism]]) ይሁን እንጂ "ነገር ግን" ሞተ የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉሙ ለእግዚአብሔር መልስ ለመስጠት አትችልም የሚል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ልክ እንደ ሞተ ሰው ለእግዚአብሔር መልስ አትሰጥም፡፡ (ተመልከት፡ rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) ሕያው ይህ ሥጋዊ ሕይወትን ያመለክታል፡፡