am_tn/1ti/01/12.md

1.6 KiB

1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡ 12-14

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጳውሎስ ባለፉት ጊዜያት እንዴት እንደሠራ በመናገር ጢሞቴዎስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ይሆን ዘንድ ያበረታታዋል፡፡ እኔ አመሰግናለሁ "አመሰግናለሁ" ወይም "እኔ አመሰግናለሁ" ተማኝ አድርጎ ቆጥሮኛልና "ታማኝ አድርጎ ቆጥሮኝ" ወይም "ታማን እንደሆንኩ ቆጥሮ" በአገለግሎቱ ላይ ሾመኝ "እንዳገለግል ሾመኝ" ወይም "በአገልግሎት ላይ ሾመኝ" እኔን ከዚህ በፊት አሳዳጅ የነበርኩትን "በክርስቶስ ላይ ክፉ ክፉ ነገሮችን የተናገርኩትን ሰው" ወይም "እኔን ባለፉት ዘመናት ተሳዳቢ የነበርኩትን ሰው" አደገኛ ሰው "ሌሎች ሰዎችን የሚጎዳ ሰው፡፡" ይህ ሌሎች ሰዎን የመጉዳት መብት አለኝ ብሎ የሚያምን ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥ አማራጭ ትርጉም: "በኢየሱስ የማላምን በመሆኔ ምክንያት እና የማደርገውን ነገር የማላውቅ በመሆነ ከኢየሱስ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ፡፡" ምሕረትን አገኘሁ አማራጭ ትርጉም: "ኢየሱስ ምሕረት አሳየኝ" ወይም "ኢየሱስ ማረኝ" ነገር ግን ጸጋ "እና ጸጋ" ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ። "በጣም በዛ" ወይም "ከበቂ በላይ ሆነ"