am_tn/1ti/01/05.md

1.7 KiB

1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡ 5-8

የትዕዛዘቱ ግብ "የመመሪያው ግብ" ወይም "እኛ ሐዋርያት እንዲታደርጉት የነገርናችሁ ነገር" ትዕዛዝ ስርዓት፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ይህ ቃል ያለው ትርጉም ብሉይ ኪዳን ወይም ዐሥርቱ ትዕዛዛትን አይደሉም ይልቁንም በ1፡3 ላይ ፓውሎስ የሰጠውን ትዕዛዝ የሚያመለክት ነው፡፡ ፍቅር አማራጭ ትርጉም 1) የእግዚአብሔር ፍቅር (UDB) ወይም 2) ከባልንጀራ ያለህ ፍቅር፡፡ ከንጹሕ ፍቅር የተነሣ "ኃጢአት ላለማድረግ ካለ መሻት" መልካም ሕልና "ትክክለኛ ወይም የተሳሳተ ምርጫ የሚያደረግ ሕልና" በእውነት "ታማኝ" ወይም "እውነት" ወይም "ያለምንም ትምክት፡፡" ሕግ በዚህ ሥፍራ ላይ ይህ ቃል የሚያመለክተው የሙሴን ሕግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አልተረዱትም "ምንም አንኳ ባይረዱትም" ወይም "ያልተረዱት ቢሆንም እንኳ" አስረግጠው የሚናገሩት ነገር "በጠንካራ ቃላት የሚናገሩት" ወይም "በእርግጠኝነት የሚናገሩት ነገር" ይሁን እንጂ "አሁን" ሕግ መልካም እንደሆነ እናውቃለን ሕግ ጠቃም እንደሆነ እንረዳለን" ወይም "ሕግ የሚጠቅም ነገር መሆኑን እንገነዘባለን" አንድ ሰው በሕግ ጥቅም ላይ ካዋለው "ምንም በአግባቢ የሚጠቀመው ከሆነ" ወይም "ለተቀመጠለት ዓላማ ማንም የሚጠቀመው ከሆነ"