am_tn/1sa/14/40.md

1.5 KiB

እስራኤልንም ሁሉ … አለ

በዚያ የነበሩት የእስራኤል ወታደሮች ብቻ ስለሆኑ ይህ አጠቃላይነት ነው፡፡ አት፡- "በዚያ ለነበሩት የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አለ' (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)

ቱሚም ስጠን

በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ምሪት ለመቀበል ኡሪምና ቱሚም የተባሉ የተለዩ ድንጋዮች ይጠቀሙ ነበር፡፡ አት፡- "በቱሚም አማካይነት አስታውቀን' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ቱሚም

ይህ ከመጀመሪያ ቋንቋ በትውስት የተወሰደ ነው፡፡ (ቅጂ ወይም ትውስት ቃላት ተመልከት)

ሳኦልና ዮናታን በዕጣው ተለዩ፣ ሕዝቡ ግን ነፃ ሆነ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይቻላል፡፡ አት፡- ዕጣዎቹ ዮናታን ወይም ሳኦል በደለኞች እንደሆኑ ነገር ግን ሠራዊቱ በደለኛ እንዳልሆነ አመለከቱ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ከዚያም ዮናታን በዕጣው ተለየ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ከዚያም ዕጣው ዮናታን በደለኛ እንደሆነ አመለከተ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)