1.4 KiB
1.4 KiB
አጠቃለይ መረጃ
ሳኦል ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበረውን ጦርነት ለመቀጠል ፈልጓል፡፡
ከመካከላቸው አንድ እንኳ በሕይወት እንዲኖር አንተው
ለግድያው አጽንዖት ለመስጠት ይህ በአሉታዊ መንገድ ተገልጾአል፡፡ በአዎንታዊ መልኩም ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እያንዳንዳቸውን እንግደል' (ምጸት ተመልከት)
ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ
ጦርነቱን ለመቀጠል ሳኦል የሠራዊቱን ድጋፍ አግኝቶአል፡፡
ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ
በዚህ ስፍራ "ወደ እግዚአብሔር መቅረብ' እርሱን ምክር ከመጠየቅ ጋር ተያይዟል፡፡ አት፡- "ምን ማደረግ እንዳለብን እግዚአብሔርን እንጠይቅ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በእስራኤል እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?
በዚህ ስፍራ "እጅ' እነርሱን ለማሸነፍ የሚሆንን ኃይል ያመለክታል፡፡ አት፡-"እንድናሸንፋቸው አስችለን' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በዚያን ቀን ግን እግዚአብሔር አልመለሰለትም
ይህ እግዚአብሔር ሳኦልን ለመርዳት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡